إعدادات العرض
የትንሳኤ ቀን አላህ ዘንድ ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ ቅጣት የሚቀጡት እነዚያ በአላህ ፍጥረት የሚፎካከሩት ናቸው።
የትንሳኤ ቀን አላህ ዘንድ ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ ቅጣት የሚቀጡት እነዚያ በአላህ ፍጥረት የሚፎካከሩት ናቸው።
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "እቃ ክፍሌን (የተንቀሳቃሽ እንስሳ) ምስል ባለበት መጋረጃ ሸፍኜው ሳለ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኔ ዘንድ መጡ። የተመለከቱት ጊዜም ፊታቸው ተለዋውጦ ቀደዱትና እንዲህም አሉ 'ዓኢሻ ሆይ! የትንሳኤ ቀን አላህ ዘንድ ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ ቅጣት የሚቀጡት እነዚያ በአላህ ፍጥረት የሚፎካከሩት ናቸው።'" ዓኢሻም እንዲህ አለች "ቆርጠነው በርሱ አንድ ትራስ ወይም ሁለት ትራስ አደረግንበት።"
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు ไทย മലയാളം Српски Kinyarwanda Türkçe ಕನ್ನಡ Lietuviųالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤታቸው ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድ ሲገቡ እቃ የምታስቀምጥበትን ትንሽዬ ክፍል ነፍስ ያላቸው ምስሎች ባለበት መጋረጃ ሸፍናው አገኟት። የፊታቸው ቀለምም ለአላህ ብለው በመቆጣታቸው ምክንያት ተለዋውጦ መጋረጃውን አወለቁት። እንዲህም አሉ: የትንሳኤ ቀን ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ ቅጣት የሚቀጡት የአላህን ፍጥረት አስመስለው ምስል የሚያደርጉት ናቸው። ዓኢሻም እንዲህ አለች: እርሱን አንድ ትራስ ወይም ሁለት ትራስ አደረግነው።فوائد الحديث
መጥፎን ነገር በማውገዛችን ሳቢያ የሚከሰት ትልቅ ብልሽት እስከሌለ ድረስ በተመለከትነው ቅፅበት ማውገዝ እንደሚገባና ማቆየትም እንደሌለብን እንረዳለን።
የትንሳኤ ቀን ቅጣት እንደ ወንጀሉ ትልቀት ይበላለጣል።
ነፍስ ያላቸው ነገሮችን ምስል ማድረግ ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።
ምስል ማድረግ ከተከለከለባቸው ጥበቦች አንዱ ከአላህ አፈጣጠር ጋር መፎካከር ስለሆነ ነው። ይህም ምስል አድራጊው መፎካከር አሰበም አላሰበም እኩል ነው።
ከጉዳዩ የተከለከለበትን ጎን ካራቅን በኋላም በርሱ መጠቀማችን ሸሪዓ ገንዘቦችን በመጠበቅ ላይ ያለውን ጉጉት ያስረዳናል።
ነፍስ ያላቸውን ምስሎች በማንኛውም ቅርፅ ቢሆኑ እንኳ፣ ፕሮፌሽናል የሆነ ምስል ቢሆን እንኳ መፈብረክ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
التصنيفات
አላህን በጌትነቱ መነጠል