إعدادات العرض
አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስፍራ መስጂዶች ናቸው። አላህ ዘንድ እጅግ የሚጠላው ስፍራ ገበያዎች ናቸው።
አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስፍራ መስጂዶች ናቸው። አላህ ዘንድ እጅግ የሚጠላው ስፍራ ገበያዎች ናቸው።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስፍራ መስጂዶች ናቸው። አላህ ዘንድ እጅግ የሚጠላው ስፍራ ገበያዎች ናቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری বাংলা ភាសាខ្មែរالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስፍራ መስጂዶች እንደሆኑ ተናገሩ። ይኸውም የአምልኮ ቤቶችና ምስረታቸውም አላህን በመፍራት ላይ ስለሆነ ነው። አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላውም ስፍራ ገበያዎች እንደሆኑ ተናገሩ። ይኸውም በአብዛኛው ማታለል፣ መሸወድ፣ ወለድ፣ የውሸት መሃላ፣ ቃልን ማፍረስና አላህን ከማስታወስ ችላ የሚባልበት ስፍራ ስለሆነ ነው።فوائد الحديث
የመስጂዶች ክብርና ደረጃን እንረዳለን። ይህም የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው ስለሆኑ ነው።
የአላህን ውዴታ በመፈለግ መስጂዶችን አዘውትሮ በመያዝ ላይ፣ ወደ መስጂድ አብዝቶ በመመላለስ ላይና ወደ ገበያዎች ደግሞ አስፈላጊ ካልሆነ በቀር በአላህ ወደመጠላት የሚያደርሱ ሰበቦች ላይ ከመውደቅ ለመራቅ ሲባል አብዝቶ ባለመመላለስ ላይ መነሳሳቱን እንመለከታለን።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "መስጂዶች የአላህ እዝነት የሚወርድባቸው ስፍራዎች ሲሆኑ ገበያዎች ደግሞ ከዚህ ተቃራኒ ናቸው።"