إعدادات العرض
እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።
እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ መስጂድ ውስጥ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጋር ተቀምጠን ሳለ አንድ ግመል ላይ ያለ ሰውዬ ገባ። መስጂድ ውስጥ ግመሉን ካንበረከከ በኋላ አሰራት። ከዚያም ለነሱ እንዲህ አላቸው፦ "ማንኛችሁ ነው ሙሐመድ?" ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመካከላቸው ተደግፈው ነበር። "ይህ የተደገፈው ቀይ ሰውዬ ነው።" አልነው። ለሳቸውም እንዲህ አላቸው "የዐብዱል ሙጠሊብ ልጅ ሆይ!" ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "አቤት ብያለሁ" አሉት። ሰውዬውም ለነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አላቸው፦ "እኔ እጠይቆታለሁ ስጠይቆት ጠንከር አደርግቦታለሁና ውስጦ በኔ ቅር እንዳይሰኝ።" እሳቸውም፦ "የፈለግከውን ጠይቅ!" አሉት። እሱም፦ "በአንተና ከአንተ በፊት ለነበሩት ጌታ በሆነው እጠይቅሀለሁ! አላህ ነውን ወደ ሰዎች ባጠቃላይ የላከህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። እሱም ቀጥሎ "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን በቀንና በምሽት አምስት ሶላቶች እንድንሰግድ ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። አሁንም ቀጥሎ "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን ከአመት ይህንን ወር እንድንፆም ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። አሁንም በመቀጠል "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን ይህንን ምፅዋት ከሀብታሞቻችን ወስደህ ለድሀዎቻችን እንድታከፋፍል ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም "አዎን" አሉት። ሰውዬውም፦ "ይዘውት በመጡት አምኛለሁ፤ ከኋላዬ ካሉ ህዝቦቼ የተላኩኝ መልክተኛ ነኝ። እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።"
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Español Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe Bosanski සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa മലയാളം తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া Shqip دری Ελληνικά Български Fulfulde Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek नेपाली Moore Kurdî Wolof Soomaali Français Oromoo Azərbaycan Tagalog Українська தமிழ் bm Deutsch ქართული Português Македонски Magyar Lingala Русскийالشرح
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-፦ መስጂድ ውስጥ ሰሐቦች ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጋር ተቀምጠው ሳለ ድንገት አንድ ግመል ላይ ያለ ሰውዬ ገባ። ግመሉን ካንበረከከ በኋላም አሰራት። ከዚያም "ማንኛችሁ ነው ሙሐመድ?" በማለት ጠየቃቸው። ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሰዎች መሀል ተደግፈው ነበር። "ይህ የተደገፈው ቀይ ሰውዬ ነው።" አልነው። ሰውዬውም ለርሳቸው፦ "የዐብዱል ሙጠሊብ ልጅ ሆይ!" አላቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለርሱ "ሰምቸሀለሁ ጠይቅ እመልስልሀለሁ።" አሉት። ሰውዬውም ለነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "እኔ እጠይቆታለሁ ስጠይቆት ጠንከር አደርግቦታለሁና ውስጦ በኔ ቅር እንዳይሰኝ።" አላቸው። ማለትም "በኔ እንዳይቆጡ በኔም መጨናነቅ እንዳያገኞት።" እሳቸውም፦ "የምትፈልገውን ጠይቅ" አሉት። እሱም "በእርሶና ከእርሶ በፊት ለነበሩት ጌታ በሆነው እጠይቆታለሁ! አላህ ነውን ወደ ሰዎች የላኮት?" አላቸው። እውነትነቱን ለማፅናት "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። ሰውዬውም፦ "በአላህ ስም እማፀኖታለሁ! አላህ ነውን በቀንና በምሽት አምስት ሶላቶች እንድንሰግድ ያዘዞት?" አላቸው። (ግዴታ ሶላቶችን) "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። "በአላህ ስም እማፀኖታለሁ! አላህ ነውን ከአመት ይህንን ወር እንድንፆም ያዘዘህ?" አላቸው። (ማለትም የረመዳንን ወር) "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን ይህንን ምፅዋት ከሀብታሞቻችን ወስደህ ለድሀዎቻችን እንድታከፋፍል ያዘዘህ?" አላቸው። (ዘካ ለማለት ነው።) ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። ይህኔ ዺማም ሰለመ። ለነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ህዝቦቹን ወደ ኢስላም እንደሚጣራ ነገራቸው። ቀጥሎ ራሱን ከበኑ ሰዕድ ቢን በክር የሆነ ዺማም ቢን ሠዕለባህ እንደሆነ በመናገር አስተዋወቃቸው።فوائد الحديث
የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን መተናነስ፤ ሰውየው በርሳቸውና በባልደረቦቻቸው መካከል መለየት ተስኖት ነበር።
የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰናይ ምግባር ፣ ለጠያቂው ለስለስ ብለው መመለሳቸው፣ መልካም አመላለስ ጥሪ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከሚያደርጉ ሰበቦች አንዱ መሆኑን፤
ሰውን በንጣት፣ በቅላት፣ በርዝመት፣ በእጥረትና በመሳሰሉት ማነወር በማይታሰብበትና ሰውዬው በማይጠላው መገለጫው ማሳወቅ እንደሚፈቀድ፤
ካፊር ለጉዳይ መስጂድ መግባት እንደሚፈቀድለት፤
በሐዲሡ ውስጥ ሐጅ ያልተጠቀሰው ምናልባት ሰውዬው በመጣበት ወቅት ሐጅ ግዴታ ያልተደረገ ሆኖ ሊሆን ይችላል።
በመስለሙ ብቻ ህዝቦቹን ለመጣራት መጓጓቱ ሰሐቦች ሰዎችን በመጣራት ላይ ያላቸውን ጉጉት ያስረዳናል።