إعدادات العرض
የሰይጣንን ተንኮል ወደ ጉትጎታ የመለሰው አላህ ምስጋና ይገባው።" አሉ።
የሰይጣንን ተንኮል ወደ ጉትጎታ የመለሰው አላህ ምስጋና ይገባው።" አሉ።
ኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለዋል፦ አንድ ሰው ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመምጣት እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን እሱን ከመናገር ይልቅ አመድ መሆን የሚያስደስተውን ነገር በነፍሱ ውስጥ ይሰማዋል።" እርሳቸውም፦ "አላሁ አክበር አላሁ አክበር የሰይጣንን ተንኮል ወደ ጉትጎታ የመለሰው አላህ ምስጋና ይገባው።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድና ነሳኢ በኩብራ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Español Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe Bosanski සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa മലയാളം తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া Shqip دری Ελληνικά Български Fulfulde Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy or Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek नेपाली Moore Kurdî Oromoo Wolof Soomaali Français Tagalog Azərbaycan Українська bm தமிழ் Deutsch ქართული Português mk Magyar فارسیالشرح
አንድ ሰው ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመምጣት እንዲህ አለ፦ የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን በነፍሱ ውስጥ የሚመላለስ ነገርን በውስጡ ይሰማዋል። ነገር ግን እሱን ከመናገር ይልቅ አመድ መሆን እስኪመኝ ድረስ እሱን መናገር ይከብደዋል። መልክተኛውም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁለት ጊዜ ተክቢር በማሰማት የሰይጣንን ተንኮል ወደ ጉትጎታ ብቻ በመመለሱ አላህን አመሰገኑ።فوائد الحديث
ሰይጣን፥ አማኞችን ከአማኝነት ወደ ክህደት ለመለወጥ በጉትጎታው እንደሚጠባበቃቸው መገለፁ።
ሰይጣን የኢማን ባለቤቶች ላይ ከጉትጎታ የዘለለ ምንም ነገር ማድረግ አለመቻሉ፤ በኢማን ባለቤቶች ላይ ደካማ አቅም ያለው መሆኑን ይገልፅልናል።
አማኝ ከሰይጣን ጉትጎታ መሸሽና መከላከል የሚገባው መሆኑን።
አስደሳች ነገር ወይም የሚያስደንቀንና የመሳሰሉት አጋጣሚዎች ሲያጋጥሙን ተክቢር ማለት የተደነገገ መሆኑ።
አንድ ሙስሊም ግራ ያጋባውን ጉዳይ ሁሉ የእውቀት ባለቤቶቹን መጠየቅ የተደነገገ መሆኑን እንገነዘባለን።