ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች።

ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች።

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች። መልካም ካልሆነች ደግሞ "ወዬውላት የት ነው ይዛችኋት የምትሄዱት?" ትላለች። ከሰው በቀር ያለ ነገር ሁሉ ድምጿን ይሰማል። የሰው ልጅ ቢሰማው ኖሮ ራሱን ስቶ ይወድቅ ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጀናዛ ቃሬዛ ላይ የተቀመጠ ጊዜና ሰዎችም ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ መልካም ከሆነች ከፊት ለፊቷ ፀጋዎችን ስለምትመለከት "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች። መልካም ካልሆነች ደግሞ ከፊት ለፊቷ ቅጣትን ስለምትመለከት በሚያወግዝ ድምፅ "ወይ ጥፋቷ! የት ነው ይዛችኋት የምትሄዱት?!" ትላለች። ከሰው በቀር ሁሉ ነገር ድምጿን ይሰማታል። ሰው ቢሰማው ኖሮ የሚሰማው ነገር ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ራሱን ይስት ነበር አሉ።

فوائد الحديث

መልካም ሆኖ የሞተ ሰው ከመቀበሩ በፊት ብስራቶችን ይመለከታል። ከሀዲ ግን ትዕግስት ያጣል። ከዚህ በተቃራኒ የሆነን ነገርም ይመለከታል።

አንዳንድ ድምጾች ከሰው በቀር ያሉ ፍጡራን ይሰሙታል። የሰው ልጅ ግን ሊሰማው አይችልም።

ጀናዛን የመሸከም ሱናው ወንዶች በትከሻዎቻቸው ላይ መሸከማቸው ነው፤ ሴቶችን አይመለከትም። ምክንያቱም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሴቶች ጀናዛን መከተላቸውን ስለከለከሏቸው ነው።

التصنيفات

የቀብር (የበርዘኽ) ህይወት