ፀሀይ በመግቢያዋ እስክትወጣ ድረስ ሰዓቲቱ አትቆምም። ከመግቢያዋ የወጣችና ሰዎች የተመለከቷት ጊዜ ሁሉም ያምናሉ

ፀሀይ በመግቢያዋ እስክትወጣ ድረስ ሰዓቲቱ አትቆምም። ከመግቢያዋ የወጣችና ሰዎች የተመለከቷት ጊዜ ሁሉም ያምናሉ

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ፀሀይ በመግቢያዋ እስክትወጣ ድረስ ሰዓቲቱ አትቆምም። ከመግቢያዋ የወጣችና ሰዎች የተመለከቷት ጊዜ ሁሉም ያምናሉ። ይህም {ከዚህ በፊት አማኝ ያልሆነችን ነፍስ እምነትዋ ወይም በእምነትዋ (ጊዜ) በጎ ያልሠራችን (ነፍስ ጸጸትዋ) አይጠቅማትም።} [አል አንዓም: 158] የተባለበት ወቅት ነው። ሰዓቲቱ ሁለት ሰዎች ሊገበያዩ ልብሶቻቸውን ዘርግተው ሳይገበያዩም ሳይሰበስቡትምም (ድንገት) ትከሰታለች፤ ሰዓቲቱ ሰውዬው ያለበውን ወተት (ለመጠጣት) እንደዞረ ሳይጠጣው (ድንገት) ትከሰታለች፤ ሰዓቲቱ ሰውዬው ምንጩን እያስተካከለ ከሱ ሳይጠጣ (ድንገት) ትከሰታለች፤ ሰዓቲቱ አንዳችሁ ጉርሻውን ወደ አፉ አስጠግቶ ሳይበላት (ድንገት) ትከሰታለች።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከትላልቆቹ የቂያማ ምልክቶች መካከል አንዱ የሆነውን ፀሀይ ከምስራቅ መውጣቷን ቀይራ ከምዕራብ እንደምትወጣ ተናገሩ። ሰዎች በሚያዩዋት ጊዜም ሁሉም ያምናሉ። በዚህ ጊዜ ግን ለከሀዲ ኢማኑ አይጠቅመውም፣ መልካም ሥራም ሆነ ተውበትም አይጠቅመውም። ቀጥለው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰዎች በዕለትተለት ሁኔታቸውና የህይወት ጉዳያቸው ላይ ሳሉ ቂያማ ድንገት እንደምትመጣ ተናገሩ። ሰዓቲቱ ሻጭና ገዢ ልብሶቻቸውን ለመለዋወጥ ዘርግተው ሳይሻሻጡም ሳይጠቀልሉትም ትከሰታለች። ሰዓቲቱ ሰውዬው የታለበ የግመል ወተቱን ይዞ ሳይጠጣው ትከሰታለች። ሰዓቲቱ ሰውዬው ምንጩን እያስተካከለ በጭቃ እያበጀው ምንም ሳይጠጣ ከሱ ትከሰታለች። ሰዓቲቱ ሰውዬው ወደ አፉ ጉርሻውን ሊበላ እንዳነሳው ሳይበላው ትከሰታለች።

فوائد الحديث

እስልምናና ተውበት ፀሀይ ከመግቢያዋ እስካልወጣች ድረስ ተቀባይነት አላቸው።

ለሰዓቲቱ በኢማንና መልካም ሥራ መዘጋጀት እንደሚገባ መነሳሳቱ ምክንያቱም ሰዓቲቱ በድንገት ስለምትከሰት።

التصنيفات

የቀብር (የበርዘኽ) ህይወት, የአንቀፆች ተፍሲር (ማብራሪያ)