የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።

የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።" "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የምድር እሳት ለቅጣት) በቂ ነበረች’እኮ" ተባሉ። እሳቸውም፦ "የጀሀነም እሳት ከምድር እሳት በስልሳ ዘጠኝ ክፍል እንድትበልጥ ተደርጋለች። ሁሉም ክፍል የምድር እሳት አምሳያ ሀሩርነት (አቃጣይነት) ነው ያላቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የዱንያ እሳት ከሰባ የጀሀነም እሳት ክፍል አንዷ ክፍል መሆኗን ተናገሩ። የአኺራ እሳት ከዱንያ እሳት በስልሳ ዘጠኝ እጥፍ የማቃጠል ደረጃዋ ይበልጣል። እያንዳንዱ የጀሀነም ክፍል ከዱንያ እሳት አቃጣይነት ጋር እኩል ነው። "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጀሀነም ውስጥ የሚገቡን ለመቅጣት የዱንያ እሳት’እኮ በቂ ነበረች።" ተባሉ። እርሳቸውም "የጀሀነም እሳት ከዱንያ እሳት በስልሳ ዘጠኝ ክፍል እንድትበልጥ ተደርጓል። የእያንዳንዱ ክፍል ሀሩርነት (የማቃጠል) ኃይልም እንደ ዱንያ እሳት አምሳያ ነው።" አሉ።

فوائد الحديث

ሰዎች ወደ እሳት ከሚያደርሱ ሥራዎች እንዲርቁ ከእሳት ማስጠንቀቅ፤

የጀሀነም እሳት ትልቅነቷ፣ ቅጣቷና የሀሩርነቷን ኃይለኝነት ተረድተናል።

التصنيفات

በመጨረሻው ቀን ማመን, የጀነትና እሳት ባህሪዎች