ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል

ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል

አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል። ተጣሪም እንዲህ በማለት ይጣራል: "የጀነት ባለቤቶች ሆይ!" ተንጠራርተው ይመለከታሉ። "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። "አዎን ይህ ሞት ነው ሁሉም ተመልክቶታል።" ይላሉ። ቀጥሎ ተጣሪው እንዲህ በማለት ይጣራል "የእሳት ባለቤቶች ሆይ!" ተንጠራርተው ይመለከታሉ። "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። "አዎን ይህ ሞት ነው ሁሉም ተመልክቶታል።" ይላሉ። ይታረዳል ቀጥሎ እንዲህ ይላቸዋል "የጀነት ባለቤቶች ሆይ! (ከዚህ በኋላ) ዘላለማዊ ሕይወት እንጂ ሞት የለባችሁም። የእሳት ባለቤቶች ሆይ! (ከዚህ በኋላ) ዘላለማዊ ሕይወት እንጂ ሞት የለባችሁም።" ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን፦ {እነሱም (አሁን) በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ ነገሩ በሚፈረድበት ጊዜ የቁጭቱን ቀን አስፈራራቸው።} [መርየም: 39] የሚለውን አንቀፅ አነበቡ። "እነዚህ በዱንያ ዝንጋቴ ውስጥ ናቸው።" {እነሱም የማያምኑ ናቸው።} [መርየም: 39]"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን ሞት ጥቁርና ነጭ በሆነ ወንድ በግ ተመስሎ ተይዞ እንደሚመጣ አብራሩ። "የጀነት ባለቤቶች ሆይ!" ተብሎ ይጠራል። አንገቶቻቸውንና ትከሻዎቻቸውን በመለጠጥ ጭንቅላታቸውንም በማንጠራራት ይመለከታሉ። ለነሱም "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። እነሱም "አዎን ይህ ሞት ነው። ሁሉም አይቶታል ያውቀዋል።" ይላሉ። ከዚያም ተጣሪው "የእሳት ባለቤቶች ሆይ!" በማለት ይለፍፋል። አንገቶቻቸውንና ትከሻዎቻቸውን በመለጠጥ ጭንቅላታቸውንም በማንጠራራት ይመለከታሉ። ለነሱም "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። እነሱም "አዎን ይህ ሞት ነው። ሁሉም አይቶታል።" ይላሉ። ሙክቱ ይታረዳል ከዚያም ተጣሪው፦ "የጀነት ባለቤቶች ሆይ! እጣፈንታችሁ ያለሞት ዘውትርና ዘላለም መኖር ነው። የእሳት ባለቤቶች ሆይ! እጣፈንታችሁ ያለሞት ዘውትርና ዘላለም መኖር ነው።" ይላቸዋል። ይህም ለአማኞች ተጨማሪ ፀጋ ለከሀዲያን የቅጣት አለንጋ እንዲሆን ነው። ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ይህን አንቀፅ አነበቡ። {እነሱም (አሁን) በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ እነሱም የማያምኑ ሲኾኑ ነገሩ በሚፈረድበት ጊዜ የቁጭቱን ቀን አስፈራራቸው።} [መርየም: 39] የትንሳኤ ቀን በጀነትና እሳት ባለቤቶች መሀል ይፈረዳል። ሁሉም ወደሚዘወትርባት ይገባል። ወንጀለኛ በጎ ባለመሥራቱ ይፀፀታልም ይቆጫልም። መልካም ከመስራት ያጓደለም ባለመጨመሩ ይቆጫል።

فوائد الحديث

የሰው ልጅ በመጪው ዓለም መመለሻው ጀነት ውስጥ ወይም እሳት ውስጥ መዘውተር ነው።

ስለ ትንሳኤ ቀን መከራ ከባድ ማስፈራሪያ መምጣቱ። እሱ የቁጭትና ፀፀት ቀን ነው።

የጀነት ባለቤቶች ደስታ እንደሚዘወትር፤ የእሳት ባለቤቶች ሀዘንም እንደሚዘወትር መገለፁ።

التصنيفات

በመጨረሻው ቀን ማመን, የጀነትና እሳት ባህሪዎች, የአንቀፆች ተፍሲር (ማብራሪያ)