إعدادات العرض
ከሰዓቲቱ (ቂያማ) ምልክቶች መካከል ዕውቀት ይነሳል፣ መሀይምነት ይስፋፋል፣ ዝሙት ይበረክታል፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት ይበዛል፣ ለሀምሳ ሴቶች አንድ (ወንድ) አስተዳዳሪ እስኪሆን ድረስ…
ከሰዓቲቱ (ቂያማ) ምልክቶች መካከል ዕውቀት ይነሳል፣ መሀይምነት ይስፋፋል፣ ዝሙት ይበረክታል፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት ይበዛል፣ ለሀምሳ ሴቶች አንድ (ወንድ) አስተዳዳሪ እስኪሆን ድረስ ወንዶች አንሰው ሴቶች ይበዛሉ።
አነስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ "ከኔ ውጪ ማንም የማይነግራችሁን ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የሰማሁትን አንድ ሐዲሥ እነግራቹሀለሁ። የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ "ከሰዓቲቱ (ቂያማ) ምልክቶች መካከል ዕውቀት ይነሳል፣ መሀይምነት ይስፋፋል፣ ዝሙት ይበረክታል፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት ይበዛል፣ ለሀምሳ ሴቶች አንድ (ወንድ) አስተዳዳሪ እስኪሆን ድረስ ወንዶች አንሰው ሴቶች ይበዛሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Español Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe Bosanski සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa മലയാളം తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া Shqip دری Ελληνικά Български Fulfulde Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy or Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek नेपाली Moore Kurdî Oromoo Wolof Soomaali Français Azərbaycan Tagalog Українська bm தமிழ் ქართული Deutsch Português Македонски Magyar فارسی Русский 中文الشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የቂያማን መቅረብ ከሚያመላክቱ ነገሮች መካከል የሸሪዐ ዕውቀት መነሳቱን ገለፁ። ይህም የሚሆነው ዑለሞች በመሞታቸው ነው። የዚህም ውጤት የመሀይምነት መሰራጨትና መብዛትን፣ የፀያፍ ድርጊቶችና ዝሙት መስፋፋትን፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት መብዛትን ያስከትላል። ለሀምሳ ሴቶች ጉዳይ የሚያስፈፅመውና የሚያስፈልጋቸውን ነገር ለማሟላት ኃላፊነት የሚወስደው አንድ ወንድ እስኪሆን ድረስ የወንዶች ቁጥር ሲመነምን የሴቶች ቁጥር ደግሞ ይጨምራል።فوائد الحديث
ጥቂት የቂያማ ምልክቶች መገለፃቸው።
ቂያማ የምትከሰትበትን ወቅት ማወቅ አላህ የተነጠለበት ከሆኑ የሩቅ ዕውቀቶቹ መካከል አንዱ ነው።
ሸሪዐዊ ዕውቀትን ከመጥፋቱ በፊት መማር እንደሚገባ መነሳሳቱ (መበረታታቱ)።