إعدادات العرض
{ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።}
{ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።}
ከዙበይር ቢን አልዓዋም እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል: {ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።} [አትተካሡር: 8] የሚለው አንቀፅ የወረደ ጊዜ ዙበይር እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እንመገብ የነበረው ሁለቱን ጥቁሮች ተምርና ውሃ ነው። ስለማንኛው ድሎት ነው የምንጠየቀው?" እሳቸውም "እርሱኑ ሳይሆን አይቀርም የምትጠየቁት።" አሉት።
[ሐሰን ነው።] [ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली മലയാളം Bosanski Italiano ಕನ್ನಡ Kurdî Oromoo Română Shqip Soomaali Српски Українська Wolof Tagalog Moore Malagasy தமிழ் Azərbaycan فارسی ქართული 中文 Magyarالشرح
ተከታዩ አንቀፅ በወረደ ጊዜ: {ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።} ማለትም አላህ በናንተ ላይ ለዋለላችሁ ፀጋ ማመስገናችሁን የምትጠየቁ ናችሁ። ዙበይር ቢን አልዓዋም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ስለማንኛው ድሎት ነው የምንጠየቀው? እነዚህ ሁለት ፀጋዎች ለመጠየቅ የሚያነሳሱ አይደሉም'ኮ እነርሱም ተምርና ውሃ ናቸው።" ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "እናንተ በዚህ ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ከመሆናችሁም ጋር ስለነዚህ ፀጋዎች ትጠየቃላችሁ። እነዚህ ሁለቱም ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎቹ መካከል ናቸውና።" አሉ።فوائد الحديث
በፀጋዎች ላይ አላህን ማመስገን እንደሚገባ ጠንከር ባለ መልኩ መምጣቱን እንረዳለን።
ትንሽም ይሁን ብዙ ፀጋ የትኛውም ባሪያ የትንሳኤ ቀን ስለርሱ የሚጠየቅበት መሆኑን እንረዳለን።