إعدادات العرض
ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።
ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ «ጀነት ውስጥ የአንዳችሁ ትንሹ ደረጃ አላህ ለርሱ "ተመኝ" ይለዋል። እርሱም ደጋግሞ ይመኛል። አላህም ለርሱ "ተመኘህን?" ይለዋል። እርሱም "አዎን" ይላል። አላህም ይለዋል: "ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Hausa Kurdî தமிழ் অসমীয়া Nederlands Kiswahili ไทยالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጀነት ለገባ ሰው የሚሰጠው ትንሹና ዝቅተኛው ደረጃና ስፍራ አላህ ለርሱ እንዲህ ይለዋል: "ተመኝ" ከሚመኘው ሁሉ አንድም ነገር ሳያስቀር ይጠቅሳል። ደጋግሞም ይመኛል። አላህም ለርሱ እንዲህ ይለዋል: "ተመኘህን?" እርሱም "አዎን" ይላል። አላህም "የተመኘኸውንና ከተመኘኸው ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።" ይለዋል።فوائد الحديث
የጀነት ሰዎች ደረጃ እንደሚበላለጥ እንረዳለን።
የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ቸርነት ትልቅ መሆኑ መገለፁን እንረዳለን።
የጀነት ፀጋ በውስን ነገር ላይ አይገደብም። ይልቁንም አንድ አማኝ ጀነት ውስጥ የተመኘውንና ነፍሱ የፈለገችውን ሁሉ ያገኛል። ይህም ከአላህ በሆነ ችሮታ፣ ቸርነትና ደግነት ነው።