إعدادات العرض
የትንሳኤ ቀን ፀሐይ ወደ ፍጡራን የአንድ ሚል (ማይል) ያህል ትቀርባለች።
የትንሳኤ ቀን ፀሐይ ወደ ፍጡራን የአንድ ሚል (ማይል) ያህል ትቀርባለች።
ከሚቅዳድ ቢን አስወድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "የትንሳኤ ቀን ፀሐይ ወደ ፍጡራን የአንድ ሚል (ማይል) ያህል ትቀርባለች።" ሱለይም ቢን ዓሚርም እንዲህ አለ "በአላህ እምላለሁ! እርሳቸው ሚል በማለት የፈለጉት የምድር ርቀት መለኪያውን ይሁን ወይስ ዐይን መኳያ እቃውን ይሁን ምን እንደፈለጉበት አላውቅም።" ነቢዩ እንዲህም ብለዋል "ሰዎችም እነደየስራቸው መጠን በላብ ይጠመቃሉ። ከነርሱ መካከል ላቡ እስከቁርጭምጭሚቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱ መካከል እስከጉልበቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱ መካከል እስከመታጠቂያው ድረስ የሚሆንም አለ፤ ከነርሱ መካከልም ላቡ የሚለጉመው አለ።" ብለው የአላህም መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በእጃቸው ወደአፋቸው ጠቆሙ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Tiếng Việt অসমীয়া Nederlands Kiswahili සිංහල ไทยالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የትንሳኤ ቀን ፀሐይ ወደ ፍጡራን ከጭንቅላታቸው በላይ የማይል ያህል እንደምትቀርብ ተናገሩ። ታቢዒዩ ሱለይም ቢን ዓሚርም እንዲህ አለ: በአላህ እምላለሁ! የአላህ መልክተኛ ሚል የሚለው ቃል ከሚሰጠው ሁለት ትርጓሜዎች የትኛውን እንደፈለጉበት አላውቅም። የምድር ርቀት መለኪያውን ማይል ነው ወይስ አይን መኳያውን ሚል ነው የፈለጉበት የሚለውን አላውቅም። እንዲህም አሉ: "በስራቸው ልክም በላብ ውስጥ ይጠመቃሉ። ከነርሱ መካከል ላቡ እስከቁርጭምጭሚቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱም መካከል ላቡ እስከጉልበቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱም መካከል ላቡ እስከሽርጥ መታጠቂያው እስከ ወገቡ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱም መካከል ላቡ እስከ አፉ ድረስ የሚሆንና መናገር የሚከለክለው አለ።" ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህንን ብለው በእጃቸው ወደ አፋቸው ጠቆሙ።فوائد الحديث
የትንሳኤ ቀን የሚከሰቱ አስደንጋጭ ክስተቶች መገለጻቸውና ከነርሱም መስፈራራቱን እንረዳለን።
የትንሳኤ ቀን ሰዎች በመቆሚያ ስፍራ ላይ እንደየስራዎቻቸው ልክ በጭንቅ ውስጥ እንደሚሆኑ እንረዳለን።
ወደ መልካም ተግባራት መነሳሳቱንና ከመጥፎ ተግባራት ደግሞ ማስፈራሪያ መምጣቱን እንረዳለን።
التصنيفات
የመጨረሻው ህይወት