إعدادات العرض
ዘመኑ እስኪጣበብ ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።
ዘመኑ እስኪጣበብ ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ዘመኑ እስኪጣበብ ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም። አመቱ እንደ ወር ይሆናል፤ ወሩ እንደ ሳምንት ይሆናል፤ ሳምንቱም እንደ ቀን ይሆናል፤ ቀኑም እንደ ሰአት ይሆናል፣ ሰአቱም የተምር ዛፍ (ዘንባባ) ቅጠል እንደሚቃጠልበት ጊዜ (ያጠረ) ይሆናል።"
[ሶሒሕ ነው።] [አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە සිංහල हिन्दी Hausa Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Türkçe Tiếng Việt नेपाली Malagasy Kinyarwanda తెలుగు Bosanski Lietuvių Oromoo Română മലയാളം Nederlands Soomaali Српски Kurdî Українська Deutsch ಕನ್ನಡ Wolof Moore Shqip Português ქართული Azərbaycan 中文 Magyar فارسیالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰአቲቱ ምልክቶች መካከል አንዱ የጊዜ መቀራረብ መሆኑን ተናገሩ። ዓመቱ ልክ እንደ ወር ያልፋል፤ ወሩም ልክ እንደ ሳምንት ያልፋል፤ ሳምንቱም ልክ እንደ ቀን ያልፋል፤ ቀኑም ልክ አንድ ሰዓት እንደሚያልፈው ያልፋል፤ ሰአቱም የተምር ዛፍ (ዘንባባ) ቅጠሉ በሚቃጠልበት ሀይለኛ ፍጥነት ልክ ቶሎ ያልፋል።فوائد الحديث
ከሰዓቲቱ ምልክቶች መካከል አንዱ የወቅት በረከት መነሳት ወይም ጊዜ መፍጠኑ ነው።
التصنيفات
የቀብር (የበርዘኽ) ህይወት