የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! መጠጫ እቃው ከሰማይ ከዋክብት ቁጥር የበዛ ነው።

የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! መጠጫ እቃው ከሰማይ ከዋክብት ቁጥር የበዛ ነው።

አቡ ዘር -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የኩሬው መጠጫ እቃ ምንድነው?" አልኳቸው። "የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! መጠጫ እቃው ከሰማይ ከዋክብት ቁጥር የበዛ ነው። ንቁ! ይህም ከደመና የፀዳ የሌሊት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ከሚታዩት የከዋክብት ቁጥር የበዛ ነው። የጀነት እቃ ነው። ከእርሱ የጠጣም ለመጨረሻ ጊዜ ከነበረበት ጥም ውጪ አይጠማም። ከጀነት የሆኑ ሁለት አሸንዳዎች ወደ ኩሬው ውኃን ያንቧቧሉ። ከሱ የጠጣ መቼም አይጠማም። የጎኑ ስፋት እንደ አግድመቱ ከዐማን እስከ አይለህ ይደርሳል። ውኃው ከወተት እጅግ የነጣ ከማር እጅግ የጣፈጠ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን የምንጫቸው መጠጫ እቃ ከሰማይ ኮኮቦች ቁጥር እንደሚበዛ ማሉ። ይህ የሰማይ ከዋክብት ቁጥርም ጨረቃ በሌለበት ድቅድቅ ምሽት ወቅት ግልፅ ይሆናል። ምክንያቱም ጨረቃ ባበራችበት ምሽት ኮኮቦች በጨረቃዋ ብርሃን ስለሚሸፈኑ ግልፅ አይሆኑም። እንዲሁም ደመና በሌለበትም ምሽት ወቅት ነው። ምክንያቱም የደመና መኖር ኮኮቦችን ከመታየት ይከለክላል። ከጀነት እቃ ውስጥ መጠጥን የጠጣ መቼም አይጠማም። ይህም አንድ ጠጪን የሚያጋጥመው የመጨረሻ ጥም ይሆናል። ከጀነት ሁለት አሸንዳዎች ወደ ኩሬያቸው ይፈሳል። የምንጫቸው አግድመቱ የእርዝማኔው አምሳያ ነው። የኩሬያቸው ማእዘናት እኩኩል ነው። እርዝማኔው ከዐማን (ሻም ውስጥ የምትገኝ በልቃእ የምትባል ሀገር ናት።) እስከ አይለህ (በሻም ጫፍ የምትገኝ የታወቀች ከተማ ናት።) የሚደርስ ርቀት ያክል ነው። የኩሬያቸው ውኃ ከወተት እጅግ የበዛ ንጣት ያለው ሲሆን ጣእሙም ከማር ጣእም ጥፍጥና የበለጠ እጅግ ጣፋጭ ነው።

فوائد الحديث

ሐውድን (ኩሬ) እና በውስጡ ያለውን የተለያዩ ፀጋዎች ማፅደቅ፤

የኩሬያቸው ግዝፈት፣ እርዝማኔውና ጎኑን፣ የመጠጫ እቃዎቹን መብዛት አውቀናል።

التصنيفات

በመጨረሻው ቀን ማመን