إعدادات العرض
አንዳችሁ የሞተ ጊዜ ለርሱ ጧትም ማታም ማረፊያው ይቀርብለታል።
አንዳችሁ የሞተ ጊዜ ለርሱ ጧትም ማታም ማረፊያው ይቀርብለታል።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: «አንዳችሁ የሞተ ጊዜ ለርሱ ጧትም ማታም ማረፊያው ይቀርብለታል። የጀነት ነዋሪ ከሆነ የጀነት ነዋሪዎች (ማረፊያ) የእሳት ነዋሪ ከሆነም የእሳት ነዋሪዎች (ማረፊያ እየቀረበለት) "አላህ የትንሳኤ ቀን እስኪቀሰቅስህ ድረስ ይህ ነው ማረፊያህ!" ይባላልም።»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو हिन्दी Tagalog 中文 ئۇيغۇرچە Kurdî Português Tiếng Việt Kiswahili Nederlands অসমীয়া ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Hausa Română ไทย తెలుగు मराठी ភាសាខ្មែរ دریالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንድ ባሪያ የሞተ ጊዜ የቀኑ መጀመሪያና መጨረሻ ላይ ጀነት ውስጥ ወይም እሳት ውስጥ የሚገኘውን ልዩ ማረፊያውና ስፍራው ይቀርብለታል። የጀነት ነዋሪ ከሆነ የጀነት ስፍራው፤ የእሳት ነዋሪ ከሆነም የእሳት ስፍራው ይቀርብለታል። እንዲህም ይባላል: "ይህ የትንሳኤ ቀን የምትቀሰቀስበት ማረፊያህ ነው።" ይህም ለአማኞች ማስደሰቻ ሲሆን ለከሃዲያን ደሞ መቀጣጫ የሆነ ንግግር ነው።فوائد الحديث
የቀብር ቅጣትና ፀጋ እውነት እንደሆነ እንረዳለን።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "አላህን ፈሪ ለሆነ አማኝና ከሃዲ ለሆነ ሰው በዚህ መልኩ እንደሚቀርብለት ግልፅ ነው። ወንጀል የቀላቀለ አማኝም መመለሻው የሆነችው የጀነት ማረፊያው ልትቀርብለት ትችላለች።"
التصنيفات
የቀብር (የበርዘኽ) ህይወት