إعدادات العرض
አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነልዐጅዚ ወልከሰሊ ወልጁብኒ ወልቡኽሊ ወልሀረሚ ወዐዛቢል ቀብር ፤ አልሏሁምመ አቲ ነፍሲ ተቅዋሃ ወዘክኪሃ አንተ ኸይሩ መን ዘክካሃ፤ አንተ ወሊይዩሃ…
አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነልዐጅዚ ወልከሰሊ ወልጁብኒ ወልቡኽሊ ወልሀረሚ ወዐዛቢል ቀብር ፤ አልሏሁምመ አቲ ነፍሲ ተቅዋሃ ወዘክኪሃ አንተ ኸይሩ መን ዘክካሃ፤ አንተ ወሊይዩሃ ወመውላሃ፤ አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዒልሚን ላ የንፈዑ፤ ወሚን ቀልቢን ላ የኽሸዑ፤ ወሚን ነፍሲን ላ ተሽበዑ፤ ወሚን ደዕወቲን ላ ዩስተጃቡ ለሃ።" (ትርጉሙም፡ "አላህ ሆይ! እኔ ከስንፍና ፣ ከመታከት ፣ ከፈሪነት ፣ ከስስት ፣ ከመጃጀትና ከቀብር ቅጣት ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት፤ ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት፤ አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና። አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም ዕውቀት፣ አንተን ከማይፈራ ልብ፣ ከማትጠግብ ነፍስ፣ ተቀባይነት ከሌላት ዱዓም ባንተ እጠበቃለሁ።")
ከዘይድ ቢን አርቀም - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «እኔ የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ይሉ ከነበሩት ውጪ አልልም። እርሳቸው እንዲህ ይሉ ነበር: "አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነልዐጅዚ ወልከሰሊ ወልጁብኒ ወልቡኽሊ ወልሀረሚ ወዐዛቢል ቀብር ፤ አልሏሁምመ አቲ ነፍሲ ተቅዋሃ ወዘክኪሃ አንተ ኸይሩ መን ዘክካሃ፤ አንተ ወሊይዩሃ ወመውላሃ፤ አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዒልሚን ላ የንፈዑ፤ ወሚን ቀልቢን ላ የኽሸዑ፤ ወሚን ነፍሲን ላ ተሽበዑ፤ ወሚን ደዕወቲን ላ ዩስተጃቡ ለሃ።" (ትርጉሙም፡ "አላህ ሆይ! እኔ ከስንፍና ፣ ከመታከት ፣ ከፈሪነት ፣ ከስስት ፣ ከመጃጀትና ከቀብር ቅጣት ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት፤ ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት፤ አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና። አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም ዕውቀት፣ አንተን ከማይፈራ ልብ፣ ከማትጠግብ ነፍስ፣ ተቀባይነት ከሌላት ዱዓም ባንተ እጠበቃለሁ።")
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी සිංහල Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Hausa Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዱዓ መካከል "አላህ ሆይ! እኔ በአንተ እጠበቃለሁ።" ወደ አንተ እጠጋለሁ። "ከስንፍና" የሚጠቅመኝን መዘየድ ከማልችልበት "ከመታከት" የመስራት ፍላጎትን ከማጣት፤ ሰነፍ ማለት መዘየድ የማይችል ሲሆን መታከት ማለት ደግሞ መስራት አለመፈለግ ማለት ነው። "ከፈሪነት" መስራት ለሚገባኝ ወደ ፊት ከመሄድ ከመቆጠብ፤ "ከስስታምነት" መስጠት ግዴታዬ ከሆነ ከመሰሰት "ከእርጅና" ሰውነትን የሚያደክም ከሆነ መጃጀት "ከቀብር ቅጣት" እና ለቀብር ቅጣት ከሚዳርጉ ምክንያቶች በአንተ እጠበቃለሁ። "አላህ ሆይ ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት!" መልካምን ለመስራትና ወንጀልን ለመተው ግጠማት። "ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት" ከአንተ ውጪ ነፍሴን የሚያፀዳ አንድም የለምና ነፍሴን ከውዳቂና ርካሽ ስነምግባር አፅዳት። "አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና።" የነፍሴን ጉዳይ የምትቆጣጠር፣ ጌታዋ፣ ባለቤቷና እርሷን የምትጣቅመው በአንተው ፀጋ ነውና። "አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም እውቀት በአንተ እጠበቃለሁ።" የኮኮብ እውቀት፣ የጥንቆላና የድግምት እውቀት አይነቱ ወይም ለመጪው አለም ከማይጠቅም እውቀት ወይም ከማይሰራበት እውቀት በአንተ እጠበቃለሁ። "አንተን ከማይፈራ ልብም በአንተ እጠበቃለሁ።" ለአንተ ከማይዋደቅ፣ ለአንተ የማይረጋ፣ አንተን በማውሳት ከማይረጋጋ ነፍስ በአንተ እጠበቃለሁ። "ከማትጠግብ ነፍስ" አላህ በሰጣትና ከለገሳት ጥሩና ሐላል ሲሳይ ከማትብቃቃ ነፍስ በአንተ እጠበቃለሁ። "ተቀባይነት ከሌላት" ተመላሽ ከሆነች "ዱዓም" በአንተ እጠበቃለሁ።"فوائد الحديث
ሐዲሡ ውስጥ ከተጠቀሱት እነዚህ ነገሮች መጠበቅ ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን።
አላህን በመፍራትና እውቀትን በማሰራጨትና በእውቀት በመስራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ጠቃሚ እውቀት ማለት ነፍስን የሚያጠራ የአላህን ፍራቻ ነፍስ ውስጥ የሚፈጥርና ከነፍሱ ተነስታ ወደ ሁሉም አካላቶቹ የሚሄድን የአላህ ፍራቻ የሚያስገኝ ነው።
የሚተናነስ ልብ ማለት የሚፈራ፣ የአላህ ስም ሲወሳ የምትርበተበት ከዚያም የምትረጋጋና የምትለዝብ ቀልብ ናት።
ለዱንያ መጓጓትና ከስሜቶቿና ከጥፍጥናዋ አለመጥገብ መወገዙን እንረዳለን። ስለዚህም ለዱንያ ጥቅም እጅግ የምትጓጓና የምትስገበገብ ነፍስ ለሰውየው የጠላቶች ጠላት ናት። ስለዚህም ነው የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከርሷ የተጠበቁት።
ሰውዬው ዱዓን ተመላሽ ከሚያደርጉና ተቀባይነትን ከሚያሳጡ ምክንያቶች ሊርቅ ይገባዋል።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥና ይህን የመሰሉ ቤት የሚመቱ ዱዓዎች ዑለሞች ለተናገሩት ማስረጃ ነው። እርሱም: ዱዓን ቤት በሚመቱ ንግግሮች ማድረግ የተወገዘው ያለ አቅሙ ቃላት ለመምረጥ ሲጥር ነው። ቃላት መረጣ መተናነስን፣ መዋደቅንና ስራን ለአላህ ማጥራትን ያስወግዳል። ከመዋደቅ፣ ፈላጊነትን ከማሳየትና በባዶ ልብ ዱዓ ከማድረግ ያዘናጋል። ነገር ግን ያለመጣጣር፣ የተሟላ አንደበተ ርቱዕ ለመሆን አይምሮን ሳያስጨንቁና የመሳሰሉትን ሳያደርጉ ወይም በሐዲሥ ውስጥ ተጠቅሶ የተሸመደደን ቤት የሚመታ ዱዓ ማለት ችግር የለውም። እንደውም የተሻለ ነው።"
التصنيفات
በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች