'ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ፤ አሏሁ አክበር ከቢራ፣ ወልሐምዱሊላሂ ከሢራ፣ ወሱብሓነሏሂ ረቢል ዓለሚን፣ ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐዚዚል ሐኪም በል።' አሉት።

'ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ፤ አሏሁ አክበር ከቢራ፣ ወልሐምዱሊላሂ ከሢራ፣ ወሱብሓነሏሂ ረቢል ዓለሚን፣ ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐዚዚል ሐኪም በል።' አሉት።

ከሰዕድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "አንድ የገጠር ሰው ወደ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመምጣት እንዲህ አለ: 'የምለውን ቃላት አስተምሩኝ?' እርሳቸውም 'ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ፤ አሏሁ አክበር ከቢራ፣ ወልሐምዱሊላሂ ከሢራ፣ ወሱብሓነሏሂ ረቢል ዓለሚን፣ ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐዚዚል ሐኪም በል።' አሉት። (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ብቸኛና አጋር የሌለው ነው። አላህ እጅግ ታላቅ ነው፤ ለአላህ ብዙ ምስጋና የተገባው ነው፤ የዓለማቱ ጌታ አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ በቀር ሀይልም ብልሀትም የለም።) እርሱም 'እነዚህ ቃላት ጌታዬን (የማወድስበት) ናቸው። ለኔስ (የምለምንበት)?' አላቸው። እርሳቸውም 'አላሁመጝፊር ሊ ወርሐምኒ ወህዲኒ ወርዙቅኒ። በል!' አሉት።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ማረኝ፣ እዘንልኝ፣ ምራኝ፣ ሲሳይን ለግሰኝ።)

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አንድ የገጠር ነዋሪ የሆነ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሚናገረውን ውዳሴ እንዲያስተምሩት ጠየቃቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ እንዲህ አሉት: "እንዲህ በል! "ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ" በተውሒድ የምስክር ቃል ጀመሩ። (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ብቸኛና አጋር የሌለው ነው።) "አሏሁ አክበር ከቢራ" ማለትም "አላህ ከሁሉም ነገር የበለጠ እጅግ ታላቅ ነው።" ማለት ነው። "ወልሐምዱ ሊላሂ ከሢራ" ማለትም "ለአላህ በባህሪዎቹ፣ በድርጊቶቹ፣ በማይቆጠሩ ፀጋዎቹ ብዙ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው። "ሱብሐነሏሂ ረቢል ዓለሚን" ማለትም "አላህ ከጉድለት የጠራ የፀዳ ነው።" ማለት ነው። "ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐዚዚል ሐኪም" ማለትም "በአላህ እገዛና መግጠም ካልሆነ በቀር ከአንድ ሁኔታ ወደ ሌላ ሁኔታ መለወጥ የለም።" ማለት ነው። ሰውዬውም "እነዚህ ቃላት ጌታዬን ለማውሳትና ለማላቅ ነው። ለነፍሴ የማደርገው ዱዐስ?" ብሎ ጠየቃቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ "እንዲህ በል!" አሉት። "አልላሁመጝፊርሊ" (አላህ ሆይ! ማረኝ) ወንጀሎችን በመማርና በመሸሸግ "ወርሐምኒ" (እዘንልኝ) ሃይማኖታዊና ዱንያዊ ጥቅሞችን ለኔ በማድረስ እዘንልኝ። "ወህዲኒ" (ምራኝ!) ወደ ተሻለ ሁኔታና ቀጥተኛውን መንገድ ምራኝ። "ወርዙቅኒ" (ሲሳይን ለግሰኝ!) ሐላል ገንዘብን፣ ጤናን፣ ሁሉንም መልካምና ደህንነት ለግሰኝ።

فوائد الحديث

አላህን በ"ተህሊል"፣ በ"ተክቢር"፣ በ"ተሕሚድ"ና በ"ተስቢሕ" በማውሳት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

ከዱዓእ በፊት አላህን ማውሳትና ማወደስ እንደሚወደድ እንረዳለን።

የሰው ልጅ በምርጥ ዱዓ፣ በቁርአንና በሐዲሥ በመጡ ዱንያዊና አኺራዊ መልካም ነገሮችን የሰበሰቡ በሆኑ ዱዓዎች ማድረጉ እንደሚወደድ እንረዳለን። በፈለገው ዱዓ ማድረግም ይችላል።

አንድ ባሪያ ለዱንያውና አኺራው የሚጠቅመውን ነገር በመማር ላይ መጓጓት ይገባዋል።

ምህረትን፣ እዝነትንና ሲሳይን በመፈለግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። እነዚህ ጉዳዮችም የመልካም ነገሮች መሰብሰቢያ ናቸው።

ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኡመታቸው የሚጠቅማቸውን ነገር በማስተማር ላይ መራራታቸውን እንረዳለን።

ከምህረት መለመን በኋላ እዝነትን መለመን የተወሳው ንፅህናው እንዲሟላ ነው። ምህረት ማለት ወንጀልህ መሸሸጉ፣ መታበሱና ከእሳት መዳን ሲሆን እዝነት ደግሞ መልካምን ማግኘትና ጀነት መግባት ነው። ትልቁ ስኬት ይህ ነው።

التصنيفات

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዚክር ዙሪያ ያላቸው መመሪያ, ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዚክር ዙሪያ ያላቸው መመሪያ, በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች, በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች