إعدادات العرض
አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዘዋሊ ኒዕመቲክ፣ ወተሐውዉሊ ዓፊየቲክ፣ ወፉጃአቲ ኒቅመቲክ፣ ወጀሚዒ ሰኸጢክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ፀጋህ ከመወገዱ፣ ለኔ የሰጠኸኝ ደህንነት ከመቀልበስ፣…
አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዘዋሊ ኒዕመቲክ፣ ወተሐውዉሊ ዓፊየቲክ፣ ወፉጃአቲ ኒቅመቲክ፣ ወጀሚዒ ሰኸጢክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ፀጋህ ከመወገዱ፣ ለኔ የሰጠኸኝ ደህንነት ከመቀልበስ፣ ከድንገተኛ መከራህ፣ ከአጠቃላይ ቁጣህ በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
ከዓብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዱዓ መካከል ይህ ዱዓ አንዱ ነበር: "አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዘዋሊ ኒዕመቲክ፣ ወተሐውዉሊ ዓፊየቲክ፣ ወፉጃአቲ ኒቅመቲክ፣ ወጀሚዒ ሰኸጢክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ፀጋህ ከመወገዱ፣ ለኔ የሰጠኸኝ ደህንነት ከመቀልበስ፣ ከድንገተኛ መከራህ፣ ከአጠቃላይ ቁጣህ በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Hausa Kurdî Português தமிழ் Русский Nederlands অসমীয়া Kiswahili ગુજરાતી پښتو ไทย Oromoo Română മലയാളം Deutsch नेपाली ქართულიالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአራት ነገሮች ተጠበቁ: የመጀመሪያው: (አላህ ሆይ! ፀጋህ ከመወገዱ በአንተ እጠበቃለሁ!) ከሃይማኖታዊም ከአለማዊውም ፀጋህ መወገድ በአንተ እጠበቃለሁ፤ በእስልምና ላይ መፅናትንና ፀጋን የሚያስወግድ ከሆነ ወንጀል ላይ ከመውደቅም መራቅን እጠይቅሃለሁ። ሁለተኛው: (ለኔ የሰጠኸኝ ደህንነት ከመቀልበስ) ወደ መከራ ከመለወጥ ማለት ነው። ዘውታሪ ደህንነትንና ከሁሉም በሽታዎችና ህመሞች ሰላም መሆንን እጠይቅሃለሁ። ሶስተኛው: (ከድንገተኛ መከራህ) ከባድ አደጋ ወይም መዐት ማለት ነው። መከራና ቅጣት በድንገት የመጣ ወቅትና ለተውበትና ለመመለስ ጊዜ ከሌለ ለተፈተነበት ሰው መከራው ትልቅና አደገኛ ይሆናል። አራተኛው: (ከአጠቃላይ ቁጣህ) ለቁጣህ የሚያስገድዱ ከሆኑ ምክንያቶች በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ የተቆጣህበት ሰው በርግጥም ባዶ ቀረ ከሰረ ማለት ነው። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠቅላይ የሆኑ ቃላትን የተጠቀሙት የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ቁጣ ምክንያቶች የሆኑትን ንግግሮች፣ ተግባሮችና እምነቶችን በሙሉ እንዲያጠቃልል ነው።فوائد الحديث
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደ አላህ ያላቸውን ፈላጊነት ያስረዳናል።
ይህቺ የተባረከች ዱዓ: ፀጋን ለማመስገን መገጠምንና ወንጀል ላይ ከመውደቅ ጥበቃን መፈለግን ሰብስባ ይዛለች። ወንጀል ላይ መውደቅ ፀጋን ታስወግዳለችና።
የአላህ ቁጣ ምክንያት ከሆኑ ስፍራዎች ለመራቅ መጣር እንደሚገባ እንረዳለን።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከድንገተኛ መከራ ተጠብቀዋል። ይህም አላህ ባሪያውን የቀጣው ጊዜ እራሱም መከላከል የማይችለውና ፍጡራን ባጠቃላይ ቢሰባሰቡለትም እንኳ የማይችሉት የሆነን መከራን ስለሚያሳርፍበት ነው።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ የሰጣቸው ደህንነት ከመቀልበስም ተጠብቀዋል። ይህም አላህ በደህንነቱ እርሳቸውን ከመረጣቸው የሁለቱንም አለም መልካም ተጎናፀፉ፤ የአላህ ደህንነት ከተቀለበሰ ደግሞ የሁለቱም ሀገር ጉዳት የሚደርስባቸው ስለሆነ ነው። የዚህ አለም ደህንነት ለዲንም ሆነ ለዱንያ መስተካከል ምክንያት ስለሆነ ነው።
التصنيفات
በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች