إعدادات العرض
አላህ ሆይ! እኔ ከመጥፎ ስነ ምግባራት፣ ከመጥፎ ስራዎችና ከመጥፎ ዝንባሌዎች በአንተ እጠበቃላሁ።
አላህ ሆይ! እኔ ከመጥፎ ስነ ምግባራት፣ ከመጥፎ ስራዎችና ከመጥፎ ዝንባሌዎች በአንተ እጠበቃላሁ።
ከቁጥባህ ቢን ማሊክ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ይሉ ነበር: "አላህ ሆይ! እኔ ከመጥፎ ስነ ምግባራት፣ ከመጥፎ ስራዎችና ከመጥፎ ዝንባሌዎች በአንተ እጠበቃላሁ።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ከነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና -ዱዓዎች መካከል: (አልላሁመ ኢኒ አዑዙ) አላህ ሆይ! እኔ ወደ አንተ እጠጋለሁ፣ ጥበቃህን እፈልጋለሁ። (ቢከ) ሌላውን ትቼ በአንተ ብቻ (ሚን ሙንከራቲ) አላህና መልክተኛው ከከለከሉት ፀያፍ (አልአኽላቅ) እንደ ምቀኝነት፣ ጥላቻና ኩራት ካሉ ስነ ምግባራት (ወልአዕማል) እንደመሳደብና መዝለፍ ካሉ ፀያፍ ተግባራት (ወልአህዋእ) ሸሪዓን ከሚፃረሩ ነፍስ የሚመኛቸው ከሆኑ ዝንባሌዎች (ባንተ እጠበቃለሁ) ማለት ነው።فوائد الحديث
የዚህን ዱዓ ደረጃና ተወዳጅነት እንረዳለን።
አማኝ የሆነ ሰው ውግዝ ስነምግባራትንና መጥፎ ተግባራትን ለመራቅ ይጥራል። ዝንባሌውን ከመከተልና ስሜት ላይ ከመውደቅም ይጠነቀቃል።
ስነምግባር፣ ስራዎችና ዝንባሌዎች ወደ መጥፎና ጥሩ ለሁለት እንደሚከፈሉ እንረዳለን።
التصنيفات
በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች