إعدادات العرض
አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤
አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሚያመሹና በሚያነጉ ጊዜ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይቦዝኑም ነበር። "አላሁም ኢኒ አስአሉከልዓፊያተ ፊድ-ዱንያ ወልአኺረቲ፣ አላሁም ኢኒ አስአሉከል ዐፍወ ወልዓፊየተ ፊ ዲኒ ወዱንያየ ወአህሊ ወማሊ፣ አላሁም ስቱር ዐውረቲ -አው ዓውራቲ- ወአሚን ረውዓቲ፣ አሏሁም ሕፈዝኒ ሚን በይኒ የደየ፣ ወሚን ኸልፊ፣ ወዓን የሚኒ፣ ወዓን ሺማሊ፣ ወሚን ፈውቂ፣ ወአዑዙ ቢአዞመቲክ 'አን ኡግታለ ሚን ተሕቲ"» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ በዱንያዬ፣ በመጪው አለሜ፣ በቤተሰቤና ገንዘቤ ይቅርታህንና ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ ነውሬን ወይም ነውሮቼን ሸሽግልኝ፣ ከፍርሃቴም ደህንነትን ስጠኝ፤ አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴም፣ ከኋላዬም፣ ከቀኜም፣ ከግራዬም፣ ከበላዬም ጠብቀኝ! ከበታቼ ድንገታዊ ጥቃት ከሚደርስብኝም በልቅናህ እጠበቃለሁ።) ማለት ነው።
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français සිංහල ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português Русский Nederlands অসমীয়া Tiếng Việt Kiswahili ગુજરાતી پښتو ไทย Oromoo Română മലയാളം Deutsch नेपाली Кыргызчаالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመሽና ሲነጋ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይቦዝኑም ነበር። (አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዓፊየተ) አላህ ሆይ! ከአለማዊ በሽታዎች፣ መከራዎችና ችግሮች፣ ከዲናዊ ፈተናዎችና ዝንባሌዎች ሰላም መሆንን (ፊድዱንያ ወልአኺረተ) በቅርቡም ሆነ በመጪው አለም እጠይቅሃለሁ። (አልላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዐፍው) አላህ ሆይ! ወንጀሎቼን ማበስ፣ ይቅር ማለትህን (ወልዓፊየተ) ከነውር መፅዳትን (ፊዲኒ) በሃይማኖቴ ከሽርክ፣ ከቢድዓና ከወንጀሎች፤ (ወዱንያየ) በዓለማዊ ህይወቴ ደሞ ከመከራዎች፣ ከሚያውክና ከክፋቶች (ወአህሊ) በቤተሰቤ ላይ በባለቤቴ፣ በልጆቼና ቅርብ ዘመዶቼ (ወማሊ) በገንዘቤና በስራዬ ላይ ደህና መሆንን እጠይቅሃለሁ። (አልላሁመስቱር ዐውራቲ) አላህ ሆይ! እኔ ላይ ያሉትን ነውሮች፣ ጉድለቶች፣ እንከኖችን ሸሽገኝ፤ ወንጀሌንም አብስ። (ወአሚን ረውዓቲ) ድንጋጤዬንና ፍርሃቴን ደህንነት ስጠው። (አልላሁመሕፈዝኒ) አላህ ሆይ! የሚያውኩኝንና መከራዎችን ከኔ አስወግድልኝ። (ሚን በይኒ የደየ፣ ወሚን ኸልፊ፣ ወዓን የሚኒ፣ ወዓን ሺማሊ፣ ወሚን ፈውቂ) (ከፊት ለፊቴም፣ ከኋላዬም፣ ከቀኜም፣ ከግራዬም፣ ከበላዬም) በዚህም አላህ ከሁሉም አቅጣጫዎች እንዲጠብቃቸው ጠየቁ። መከራዎችና መአቶች ወደ ሰው የሚመጡትና የሚዞሩት ከነዚህ አቅጣጫዎች መካከል በአንዱ ነውና። (ወአዑዙ ቢዐዞመቲከ አንኡግታል) በድንገት ከመያዝና ተዘናግቼ ከምጠፋ በልቅናህ እጠበቃለሁ። (ሚንተሕቲ) በመሬት መደርመስ ከመጥፋትም ባንተ እጠበቃለሁ።فوائد الحديث
መልክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመከተል እነዚህን ቃላቶች መጠባበቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
የሰው ልጅ የሃይማኖቱን ደህንነት አላህን እንዲጠይቅ እንደታዘዘው ሁሉ ለዓለማዊ ጉዳዩም እንዲጠይቅ ታዟል።
ጢቢ እንዲህ ብለዋል: «ስድስቱን አቅጣጫዎች ማጠቃለላቸው የመከራዎች መምጣት በነርሱ በኩል ስለሆነ ነው። የታች አቅጣጫን አበክረው የጠቀሱት ከታች የሚመጣ መከራ አዋራጅ ስለሆነ ነው።»
ንጋት ላይ አዝካሮችን ለመቅራት በላጩ ወቅት: ጎህ ከወጣ ጀምሮ የቀኑ መጀመሪያ ላይ ፀሃይ እስክትወጣ ድረስና ከዐስር በኋላ ፀሃይ እስክትገባ ድረስ ነው። ከዚህ በኋላም ቢል ማለትም ረፋዱ ከፍ ካለ በኋላም ቢል ይበቃለታል። ከዙህር በኋላም ቢል ይበቃለታል። ከመጝሪብ በኋላም ቢል ይበቃለታል። ይህም የዚክር ወቅት ነውና።
ዚክሩ መባል ያለበት በተለየ ወቅት እንደሆነ ማስረጃ ከጠቆመ የሱረቱል በቀራ መጨረሻ ሁለት አንቀጾችን ምሽት ላይ መቅራትን ይመስል ፀሃይ ከገባ በኋላ ምሽት ላይ ነው የሚፈፀመው።
التصنيفات
በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች