إعدادات العرض
አላህ ሆይ! እኔ በእዳ ከመሸነፍ፣ በጠላት ከመሸነፍና የጠላቶች ደስታ ምንጭ ከመሆን ባንተ እጠበቃለሁ።
አላህ ሆይ! እኔ በእዳ ከመሸነፍ፣ በጠላት ከመሸነፍና የጠላቶች ደስታ ምንጭ ከመሆን ባንተ እጠበቃለሁ።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በነዚህ ቃላቶች ዱዓ ያደርጉ ነበር: "አላህ ሆይ! እኔ በእዳ ከመሸነፍ፣ በጠላት ከመሸነፍና የጠላቶች ደስታ ምንጭ ከመሆን ባንተ እጠበቃለሁ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kurdî Português සිංහල Nederlands অসমীয়া Kiswahili ગુજરાતી پښتو ไทย Oromoo Română മലയാളം Deutsch नेपालीالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከነዚህ ጉዳዮች ጥበቃን ፈለጉ: የመጀመሪያው: (አላህ ሆይ! እኔ በአንተ እጠበቃለሁ) በሌላ በማንም ሳይሆን (በእዳ ከመሸነፍ) ከእዳ ጭንቀት፣ ችግር፤ እዳውን በመክፈልና በመዝጋት ያንተን እገዛ እጠይቅሃለሁ። ሁለተኛው: (በጠላት ከመሸነፍ) በኔ ላይ ጠላት የበላይ ከመሆንብኝና ከሚቆጣጠረኝ፤ የርሱን ጉዳት መከላከልና በርሱ ላይ ድል መቀናጀትን እጠይቅሃለሁ። ሶስተኛው: (የጠላቶች የደስታ ምንጭ ከመሆን) ሙስሊሞችን በሚያገኛቸው መከራና ችግር ደስተኛ ከመሆናቸው በአንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው።فوائد الحديث
ከእዳና ከመሳሰሉት ከአምልኮ ከሚያጠምዱና ጭንቀትን ከሚያመጡ ነገሮች ሁሉ በአላህ በመጠበቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ዕዳ በጥቅሉ ችግር የለውም። ችግር ያለው እዳ መክፈያ በሌለው ሰው ላይ ነው። በእዳ የሚሸነፈውም ይህ ነው።
የሰው ልጅ ጠላትን የሚያስደስትበትንና የሚነወርበትን ነገሮች መራቅ ይገባዋል።
ከሀዲዎች ለአማኞች ያላቸውን ጠላትነትና አማኞች ላይ መከራ መድረሱ የደስታቸው ምንጭ መሆኑ መገለፁን እንረዳለን።
የሰው ልጅ ከደረሰበት መከራ የበለጠ ጠላቶች በመከራው መደሰታቸውን ግልፅ ማድረጋቸው የበለጠ ይጎዳል።
التصنيفات
በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች