አልላሁመ ለከ አስለምቱ፣ ወቢከ አመንቱ፣ ወዐለይከ ተወከልቱ፣ ወኢለይከ አነብቱ፣ ወቢከ ኻሶምቱ፤ አልላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢዒዘቲከ፣ ላኢላሃ ኢላ አንተ አንቱዲለኒ፣ አንተልሐይዩ ለዚ…

አልላሁመ ለከ አስለምቱ፣ ወቢከ አመንቱ፣ ወዐለይከ ተወከልቱ፣ ወኢለይከ አነብቱ፣ ወቢከ ኻሶምቱ፤ አልላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢዒዘቲከ፣ ላኢላሃ ኢላ አንተ አንቱዲለኒ፣ አንተልሐይዩ ለዚ ላየሙት፣ ወልጂኑ ወልኢንሱ የሙቱን" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ላንተ እጅ ሰጥቻለሁ፤ ባንተም አምኛለሁ፤ ባንተም ላይ ተመክቻለሁ፤ ወዳንተም ተመልሻለሁ፤ ባንተ መንገድም ተሟግቻለሁ፤ አላህ ሆይ! እኔ እንዳታጠመኝ በልቅናህ እጠበቃለሁ፤ ካንተ በቀርም በእውነት የሚመለክ የለም። የማይሞት ህያው አንተው ነህ። ጋኔንም ሰውም ይሞታሉ።" ማለት ነው።

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ይሉ ነበር: "አልላሁመ ለከ አስለምቱ፣ ወቢከ አመንቱ፣ ወዐለይከ ተወከልቱ፣ ወኢለይከ አነብቱ፣ ወቢከ ኻሶምቱ፤ አልላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢዒዘቲከ፣ ላኢላሃ ኢላ አንተ አንቱዲለኒ፣ አንተልሐይዩ ለዚ ላየሙት፣ ወልጂኑ ወልኢንሱ የሙቱን" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ላንተ እጅ ሰጥቻለሁ፤ ባንተም አምኛለሁ፤ ባንተም ላይ ተመክቻለሁ፤ ወዳንተም ተመልሻለሁ፤ ባንተ መንገድም ተሟግቻለሁ፤ አላህ ሆይ! እኔ እንዳታጠመኝ በልቅናህ እጠበቃለሁ፤ ካንተ በቀርም በእውነት የሚመለክ የለም። የማይሞት ህያው አንተው ነህ። ጋኔንም ሰውም ይሞታሉ።" ማለት ነው።

[ሶሒሕ ነው።]

الشرح

ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዱዓ መካከል እርሳቸው እንዲህ ይሉ ነበር: (አልላሁመ ለከ አስለምቱ) ላንተ ታዛዥ ሆኛለሁ። (ወቢከ አመንቱ) ባንተ አረጋግጫለሁ፤ እውነት ብያለሁ። (ወዐለይከ ተወከልቱ) ባንተ ላይ ተደግፌያለሁ ተጠግቻለሁ። (ወኢለይከ አነብቱ) ወዳንተ ዞሬያለሁ፤ ተመልሻለሁ። (ቢከ ኻሶምቱ) ጠላቶችህን ተሟግቻለሁ። (አላሁመ ኢኒ አዑዙ) አላህ ሆይ እኔ እጠጋለሁ (ቢዒዘቲከ) ወደ ሀይልህና አሸናፊነትህ (ላኢላሃ ኢላ አንተ) ከአንተ ውጪ በእውነት የሚመለክ የለም። (አንቱዲለኒ) ወዳንተ ውዴታ ከመመራትና ከመገጠም እንዳታጠመኝ። (አንተል ሐይዩ ለዚ ላየሙት) የማይጠፋው ህያው ነህ። (ወልጂኑ ወልኢንሱ የሙቱን) ሰውና ጋኔን ይሞታሉ።

فوائد الحديث

የምንፈልገውን ከመጠየቃችን በፊት ሁሌም ውዳሴን ማስቀደም የተደነገገ እንደሆነ እንረዳለን።

በአላህ ላይ ብቻ መመካትና ከርሱ ጥበቃን መፈለግ ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን። ምክንያቱም እርሱ በምሉዕነት መገለጫዎች የሚገለፅ ነውና። እርሱ ብቻ ነው መጠጊያ። ፍጡራን ባጠቃላይ ደካሞችና ሞት የሚከተላቸው ናቸው። ስለዚህም በነርሱ ላይ ለመመካት ብቁ አይደሉም።

ሁሉን ያቀፉና ምንም ያላስቀሩ በሆኑት እንዲሁም እውነተኛ ኢማንና ወሰን የለሽ እርግጠኝነትን የሚገልፁ በሆኑት በነዚህ ቃላቶች ዱዓ በማድረግ የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ፈለግ መከተል ተገቢ እንደሆነ እንረዳለን።

ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "(ህያው አንተው ነህ) ማለታቸው ጥበቃ ሊፈለግበት የሚገባው አንተ ብቻ እንጂ ሌላ ማንም አይደለም። ለማለት ነው።"

التصنيفات

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዚክር ዙሪያ ያላቸው መመሪያ, በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች