إعدادات العرض
አላሁመ ኢንኒ አስአሉከል ሁዳ፣ ወትቱቃ፣ ወልዓፋፈ፣ ወልጊና" ትርጉሙም፡ "አላህ ሆይ! እኔ ቀናውን መንገድ፣ ጥንቁቅነትን፣ ጥብቅነትንና መብቃቃትን እጠይቅሃለሁ።" ማለት ነው።
አላሁመ ኢንኒ አስአሉከል ሁዳ፣ ወትቱቃ፣ ወልዓፋፈ፣ ወልጊና" ትርጉሙም፡ "አላህ ሆይ! እኔ ቀናውን መንገድ፣ ጥንቁቅነትን፣ ጥብቅነትንና መብቃቃትን እጠይቅሃለሁ።" ማለት ነው።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ይሉ ነበር: "አላሁመ ኢንኒ አስአሉከል ሁዳ፣ ወትቱቃ፣ ወልዓፋፈ፣ ወልጊና" ትርጉሙም፡ "አላህ ሆይ! እኔ ቀናውን መንገድ፣ ጥንቁቅነትን፣ ጥብቅነትንና መብቃቃትን እጠይቅሃለሁ።" ማለት ነው።
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt অসমীয়া Nederlands Kiswahili Hausa සිංහල ไทยالشرح
ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዱዓዎች መካከል ይህ ዱዓ ይገኝበታል: "አልላሁመ ኢንኒ አስአሉከል ሁዳ" አላህ ሆይ! ሐቅን የማወቅና በሐቅ የመስራት ቀጥተኛውን መንገድ እጠይቅሃለሁ። "ወትቱቃ" ትእዛዛቶችህን ለመተግበርና ክልከላዎችህን ለመራቅ የሚረዳኝን ፍራቻህን እጠይቅሃለሁ። "ወልዐፋፍ" ከማይፈቀዱና መልካም ካልሆኑ ንግግሮችና ተግባራት ጥብቅ እንድታደርገኝ እጠይቅሃለሁ። "ወልጊና" ከጌታዬ በቀር ወደ አንድም ፍጡር የማልፈልግ እስክሆን ድረስ ከፍጡራን የተብቃቃ እንድታደርገኝ እጠይቅሃለሁ።فوائد الحديث
እነዚህ ጉዳዮች የላቁ ጉዳዮች መሆናቸውን እንረዳለን። እነርሱም: ቀና መንገድ፣ ጥንቁቅነት፣ ጥብቅነትና የተብቃቃ ሰው መሆን ናቸው። እነዚህን ጉዳዮች በመላበስ ላይም መነሳሳቱን እንመረዳለን።
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለነፍሳቸው ጥቅምና ጉዳት ማምጣት አይችሉም። ይህንን የሚችለው አላህ ብቻ ነው።
ለፍጡራን መጥቀም፣ መጉዳትና መምራት የሚችለው አላህ ብቻ ነው። ከአላህ ውጪ ቅርብ መልዐክም፣ የተላከ ነቢይም ሆነ ከነርሱ ውጪ ያለ አካልም ቢሆን ማንም እነዚህን ማድረግ አይችልም።
التصنيفات
በሐዲሥ የመጡ ዱዓዎች