إعدادات العرض
የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው።
የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው።
ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው። ሽቶ ተሸካሚ ወይ ይሰጥሀል፣ ወይ ትገዛዋለህ፣ ወይ ከርሱ መልካም መአዛን ታገኛለህ። ወናፍ ነፊ ደሞ ወይ ልብስህን ያቃጥላል ወይም ከርሱ መጥፎ ሽታን ታገኛለህ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල دری অসমীয়া ไทย Tiếng Việt Svenska Yorùbá Кыргызча ગુજરાતી नेपाली Oromoo മലയാളം Română Nederlands Soomaali پښتو తెలుగు Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Malagasy Српски Moore ქართულიالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት አይነት ሰዎችን በምሳሌ ገለፁ። የመጀመሪያው አይነት: ወደ አላህ የሚጠቁም፣ ወደ አላህ ውዴታ የሚመራና በአምልኮ ላይ የሚያግዝ መልካም ጓደኛ ነው። የርሱም ምሳሌ ሽቶ እንደሚሸጥ ሰው ምሳሌ ነው። ወይ ይሰጥሀል፣ ወይ ትገዛዋለህ፣ ወይም ከርሱ መልካም መአዛን ታሸታለህ። ሁለተኛው አይነት ደግሞ ከአላህ መንገድ የሚያቅብ፣ ወንጀል በመፈፀም ላይ የሚያግዝ ፣ መጥፎ ተግባራትን የምታይበት መጥፎ ጓደኛ ነው። የሱን አይነት ሰው ወዳጅና ጓደኛ አድርገህ በመያዝህም የሚያስወቅስህ ነው። የርሱም ምሳሌ ወናፍ እንደሚያናፋ ብረት ቀጥቃጭ ነው። እርሱም ወይ በሚፈነጣጠረው እሳት ልብስህን ያቃጥላል ወይም ወደርሱ በመቅረብህ መጥፎ ሽታን ታገኛለህ።فوائد الحديث
አዳማጩ ሀሳቡ እንዲገባው ምሳሌ ማድረግ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
የመልካምና የበጎ ባለቤቶችን በመቀማመጥ ላይና የብክለትና የመጥፎ ስነ ምግባር ባለቤቶችን በመራቅ ላይ መነሳሳቱና መበረታታቱን እንረዳለን።