አይነአፋርነት ከኢማን ነው።

አይነአፋርነት ከኢማን ነው።

ከዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ሰውዬ ወንድሙን በአይነአፋርነቱ ሲወቅሰው ሰሙና 'አይነአፋርነት ከኢማን ነው።' አሉት።

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድን ሰውዬ ለወንድሙ አይነአፋርነት ማብዛት እንዲተው ሲመክረው ሰሙትና አይነአፋርነት ከኢማን መሆኑን እና ከመልካም በስተቀር ይዞ እንደማይመጣ ገለፁለት። አይነአፋርነት መልካም ድርጊት ለመስራትና እኩይ ተግባር ለመተው የሚያነሳሳ ስነምግባር ነው።

فوائد الحديث

ከመልካም ተግባር የሚከለክል ባህሪ ተወዛጋቢነት፣ ደካማነት፣ ልፍስፍስነትና ፈሪነት እንጂ አይነአፋርነት አይባልም።

ከአሏህ ሓያእ ማድረግ የሚሆነው ትእዛዛትን በመፈፀምና ክልከላትን በመተው ነው።

ከፍጡራን ሐያእ ማድረግ የሚሆነው እነሱን በማክበር፣ በሚመጥናቸው ደረጃቸው ላይ በማስቀመጥና በተለምዶ ከሚያፀይፍ ድርጊት በመራቅ ነው።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር