አንዳችሁ ከወላጆቹ ፣ ከልጁና ከሰዎች ባጠቃላይ እርሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ እኔ እስክሆን ድረስ አላመነም።'

አንዳችሁ ከወላጆቹ ፣ ከልጁና ከሰዎች ባጠቃላይ እርሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ እኔ እስክሆን ድረስ አላመነም።'

ከአነስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ከወላጆቹ ፣ ከልጁና ከሰዎች ባጠቃላይ እርሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ እኔ እስክሆን ድረስ አላመነም።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

አንድ ሙስሊም ለአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያለው ውዴታ ለእናቱ ፣ ለአባቱ ፣ ለወንድ ልጁ፣ ለሴት ልጁና ለሰዎችም ባጠቃላይ ካለው ውዴታ እስኪያስቀድም ድረስ ኢማኑ ምሉዕ አይሆንም በማለት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። ይህ ውዴታም እሳቸውን መታዘዝን፣ መርዳትንና እሳቸውን ማመፅ መተውን ያስፈርዳል።

فوائد الحديث

መልክተኛውን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መውደድና ከሁሉም ፍጡራን ውዴታ ማስቀደም ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።

የአላህን መልክተኛ ሱና መርዳትና በዚህ መንገድ ላይም ገንዘብና ነፍስን መለገስ ከተሟላ ውዴታ ምልክቶች መካከል አንዱ ነው።

መልክተኛውን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መውደድ ባዘዙት ነገር መታዘዝን ፣ በተናገሩት ማመንን፣ ከከለከሉትና ካስጠነቀቁት ነገሮች መከልከልን፣ እሳቸውን መከተልንና ቢድዓን መተው ያስፈርዳል።

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጥመት መንገድ (ወደ ቀናው) ለመመራታችን ፣ ከእሳት ለመዳናችን፣ ጀነትን ለመጎናፀፋችን ምክንያት ስለሆኑ የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሀቅ ከሁሉም ሰዎች ሀቅ የበለጠና የገዘፈ ነው።

التصنيفات

የቀልብ ተግባራት