ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን

ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን

ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን የተቸገረ ካጋጠመህ እለፈው።' (ሞተና) አላህንም ተገናኘ፤ አላህም ይቅር አለው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰዎች ጋር በመበዳደር የሚንቀሳቀስ ወይም በዱቤ የሚሸጥላቸው ስለሆነ ሰው ተናገሩ። ለሰዎች ያበደረውን ብድር ለሚቀበልለት ሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ "ተበዳሪ ዘንድ ስትሄድ እዳውን መክፈል ተስኖት ካገኘኸው እለፈው" ይህም የሚከፍልበትን ፋታ በመስጠት፣ እዳውን በመፈለግ ላይ ችክ ባለማለት ወይም ጥቂት ቢጎድልም ያለውን በመቀበል ሊሆን ይችላል። ይህንንም የሚያደርገው አሏህ የእርሱንም ወንጀል እንዲያልፍለትና ይቅር እንዲለው ከመከጀል አኳያ ነበር። በሞተም ጊዜ አሏህም ማረው፤ ወንጀሉንም ይቅር አለለት።

فوائد الحديث

ከሰዎች ጋር ባለ መስተጋብር መልካሙን መዋል፣ ይቅር ማለትና ሰው ሲቸግረው ብድሩን ማለፍ አንድ ባርያ በቂያማ እለት ከሚድንባቸው ትላልቅ ሰበቦች መካከል እንደሆነ እንረዳለን።

ለፍጡራን በጎ መዋል፣ ለአሏህ ስራን ጥርት ማድረግና እዝነቱንም መከጀል ለወንጀል መሀርታን ከሚያስገኙ ሰበቦች መካከል አንዱ መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር