በአላህ ላይ ትክክለኛውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚለግሰው ለናንተም ሲሳይን ይለግሳቹህ ነበር። (ወፍ) ተርባ ማልዳ ትወጣለች። ሆዷ (በጥጋብ) ሞልቶ ትመለሳለች።

በአላህ ላይ ትክክለኛውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚለግሰው ለናንተም ሲሳይን ይለግሳቹህ ነበር። (ወፍ) ተርባ ማልዳ ትወጣለች። ሆዷ (በጥጋብ) ሞልቶ ትመለሳለች።

ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማ: "በአላህ ላይ ትክክለኛውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚለግሰው ለናንተም ሲሳይን ይለግሳቹህ ነበር። (ወፍ) ተርባ ማልዳ ትወጣለች። ሆዷ (በጥጋብ) ሞልቶ ትመለሳለች።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዱንያዊም በዲናዊም ጉዳይ ጥቅምን በማምጣትና ጉዳትን በመከላከል ረገድ በአላህ ላይ እንድንደገፍ እያነሳሱን ነው። ምክንያቱም ከአላህ በስተቀር የሚሰጥም፣ የሚከለክልም ፣ የሚጎዳም፣ የሚጠቅምም የለምና ነው። ጥቅሞችን የሚያመጡና ጉዳቶችን የሚከላከሉ ሰበቦችን በአላህ ላይ ከእውነተኛ መመካት ጋር እንድንፈፅምም አነሳሱ። ይህንን በማንኛውም ወቅት ከፈፀምን አላህ ወፍን በንጋት የተራበች ሆና ወጥታ ከዚያም በምሽት ሆዷ ሞልቶ በመመለስ እንደሚቀልባት እኛንም ይቀልበን ነበር። ይህ የወፏ ድርጊት ያለመሳነፍና መዳከም ሲሳይን ለመፈለግ የሰራችው የሰበብ አይነት ነው።

فوائد الحديث

የመመካት ትሩፋትን ፤ መመካት ሲሳይን ከሚያመጡ መንስኤዎች መካከል ትልቁ ነው ።

መመካት ሰበቦችን ከመፈፀም ጋር አይጋጭም። ምክንያቱም እሳቸው ሲሳይ ለመፈለግ ማልዶ መውጣትና አምሽቶ መመለስ ትክክለኛውን መመካት እንደማይጣረሰው ተናግረዋልና።

ሸሪዐ ለቀልብ ተግባራት ትኩረት መስጠቱን፤ መመካት የቀልብ ተግባር ነውና።

በሰበብ ላይ ብቻ መንጠልጠል የዲን ጉድለት ሲሆን ሰበቦችን መተው ደግሞ የአይምሮ ጉድለት ነው።

التصنيفات

የቀልብ ተግባራት ትሩፋቶች