ጀሀነም ነፍስያ በምትወዳቸው ስሜታዊ ነገሮች ተጋረደች፤ ጀነት ደግሞ ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተጋረደች።

ጀሀነም ነፍስያ በምትወዳቸው ስሜታዊ ነገሮች ተጋረደች፤ ጀነት ደግሞ ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተጋረደች።

ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ረሱል የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "ጀሀነም ነፍስያ በምትወዳቸው ስሜታዊ ነገሮች ተጋረደች፤ ጀነት ደግሞ ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተጋረደች።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጀሀነም ክልክልን በመዳፈርና ግዴታን ባለመወጣት የመሰሉ ነፍስያ በምትፈልጋቸው ነገሮች መሸፈኗን መከበቧን ገለፁ። በመሆኑም የነፍስያውን ፍላጎት በዚህ ረገድ የተከተለ ለጀሀነም ተገባ። ጀነት ደግሞ ትእዛዝ ላይ በመዘውተር፣ ክልከላን በመተውና በዚሁ ላይ ትዕግስት በማድረግ በመሰሉ ነፍስያ በምትጠላቸው ነገሮች መሸፈኗንና መከበቧን አብራሩ። ስለዚህም በዚህ ረገድ በቁርጠኝነት ነፍስያውን የታገለ ለጀነት የተገባ ሆነ።

فوائد الحديث

በስሜት ላይ ለመውደቅ ሰበብ ከሚሆኑ መሰናክሎች መካከል አስቀያሚና የተወገዘ የሆነውን ነገር ነፍስያ ወዳው እስክትዘነበልለት ድረስ ሸይጧን ማስዋቡ አንዱ መሆኑን፤

ወደ ጀሀነም እሳት መዳረሻ ከመሆናቸው አንፃር ከተከለከሉ ፍላጎቶች መራቅና ወደ ጀነት የሚያደርሱ ከመሆናቸው አንፃርም የምንጠላቸው ነገሮች ላይ መታገስን መታዘዛችን ፤

ነፍስያን መታገል፣ በዒባዳ ላይም መትጋት፣ በአምልኮ ዙርያ ያሉ የምንጠላቸውና የሚያስቸግሩን ነገሮች ላይም መታገስ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።

التصنيفات

የጀነትና እሳት ባህሪዎች