ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ

ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ: ' 'ሱብሓነላሂ አልዐዚም ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰው ልጅ ያለምንም መጨናነቅና በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሆኖ ስለሚናገራቸው ሁለት ቃላቶች ነገሩን። እነሱም ምንዳቸው ሚዛን ላይ የገዘፈ፣ ጌታችን አር‐ራሕማንም የሚወዳቸው ናቸው። "ሱብሓነላሂ አልዐዚም ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ" የሚሉት ናቸው። ደረጃቸው የላቀበትም ምክንያት የአላህን የልቅናና የምሉዕነት ባህሪያት የያዙ ፤ የላቀውንና የጠራውን አላህንም ከጉድለቶች ስለሚያጠሩ ነው።

فوائد الحديث

በላጩ ውዳሴ አላህን ማጥራትና ማወደስን የሰበሰበ ውዳሴ ነው።

አላህ በጥቂት ስራ ብዙ ምንዳ መመንዳቱ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ሰፊ መሆኑን ይገልፅልናል።

التصنيفات

ልቅ የሆኑ ዚክሮች