ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።

ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።

ከጁበይር ቢን ሙጥዒም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እሱ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማቸው: "ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለቅርብ ዘመዶቹ ያለበትን ግዴታ ከመወጣት ይልቅ ዝምድናውን የቆረጠ ሰው ወይም ያወካቸውና ያስከፋቸው ጀነት ላለመግባት የተገባ ነው ብለው ተናገሩ።

فوائد الحديث

ዝምድናን መቁረጥ ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።

ዝምድናን መቀጠል በተለምዶ በሚታወቀው መልኩ ነው የሚሆነው። ቦታ፣ ዘመንና ሰዎቹ እንደመለያየታቸው ይለያያል።

ዝምድናን መቀጠል በመዘየር፣ ሶደቃ በመስጠት፣ ለነርሱ በጎ በመዋል፣ ሲታመሙ በመጠየቅ፣ በመልካም በማዘዝ፣ ከመጥፎ በመከልከልና በሌሎችም መልኩ ይፈፀማል።

ዝምድናው የሚቆረጠው ሰው እጅግ ቅርብ ዘመድ በሆነ ቁጥር ወንጀሉም እጅግ የከፋ ይሆናል።

التصنيفات

ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት, ዝምድናን የመቀጠል ትሩፋቶች