አንድ ሰው ወደ ቤቱ ሲገባ በሚገባበት ወቅትም በሚበላበት ወቅትም አላህን ካወሳ ሰይጣን (ለባልደረቦቹ) 'ማደሪያም እራትም የላችሁም።' ይላል።

አንድ ሰው ወደ ቤቱ ሲገባ በሚገባበት ወቅትም በሚበላበት ወቅትም አላህን ካወሳ ሰይጣን (ለባልደረቦቹ) 'ማደሪያም እራትም የላችሁም።' ይላል።

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰማ: "አንድ ሰው ወደ ቤቱ ሲገባ በሚገባበት ወቅትም በሚበላበት ወቅትም አላህን ካወሳ ሰይጣን (ለባልደረቦቹ) 'ማደሪያም እራትም የላችሁም።' ይላል። በሚገባ ወቅት አላህን ሳያወሳ የገባ እንደሁ ሰይጣን 'ማደሪያ አግኝታችኋል' ይላል። በሚበላበት ወቅትም አላህን ካላወሳ ደግሞ 'ማደሪያም እራትም አግኝታችኋል።' ይላል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤት በሚገባ ወቅትና ምግብ ከመመገባችን በፊት አላህን ማውሳት አዘዙ። እርሱ ቤት በሚገባ ወቅትና ምግቡን በሚጀምር ወቅት አላህን (ቢስሚላህ) በማለት ያወሳ ጊዜ ሰይጣን ለግብረ አበሮቹ "እዚህ ባለቤቱ አላህን በማውሳት ከናንተ የተጠበቀበት በሆነው ቤት ውስጥ ምንም ማደሪያም እራትም የላችሁም።" ይላቸዋል። ሰውዬው ቤቱ በሚገባ ወቅትና ምግብ በሚመገብበት ወቅት አላህን ካላወሳ ግን ሰይጣን ለግብረአበሮቹ እዚህ ቤት ውስጥ ማደሪያም እራትም እንዳገኙ ይናግራቸዋል።

فوائد الحديث

ቤት በሚገቡበትና ምግብ በሚመገቡበት ወቅት አላህን ማውሳት እንደሚወደድ እንረዳለን። የቤቱ ባለቤቶች አላህን ካላወሱ ሰይጣን ቤቶች ውስጥም ያድራል፤ ከባለቤቶቹ ምግብም ይመገባል።

ሰይጣን የሰውን ልጅ በስራው፣ በእንቅስቃሴውና በሁሉም ጉዳዩ ይጠባበቀዋል። ሰው ከዚክር (ከውዳሴ) በተዘናጋ ጊዜ ሸይጧንም ከርሱ የሚፈልገው ፍላጎቱን ያገኛል።

ዚክር (ውዳሴ) ሰይጣንን እንደሚያባርር እንረዳለን።

ሁሉም ሰይጣን በንግግሩ የሚደሰቱና ትእዛዙን የሚከተሉት ተከታይና ወዳጆች እንዳሉት እንረዳለን።

التصنيفات

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዚክር ዙሪያ ያላቸው መመሪያ, ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዚክር ዙሪያ ያላቸው መመሪያ, አላህን የማውሳት ጥቅሞች, አላህን የማውሳት ጥቅሞች, ከቤት ሲወጣና ሲገባ የሚባሉ ዚክሮች, ከቤት ሲወጣና ሲገባ የሚባሉ ዚክሮች