መልካም ነገሮች ሁሉ ምፅዋት ናቸው።

መልካም ነገሮች ሁሉ ምፅዋት ናቸው።

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "መልካም ነገሮች ሁሉ ምፅዋት ናቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

በንግግርም ይሁን በተግባር ለሌሎች የምንውለው በጎነትና ጥቅም ሁሉ ምፅዋት እንደሚሆንና በሱም ምንዳና አጅር እንደምናገኝበት ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።

فوائد الحديث

ምፅዋት የሰው ልጅ ከገንዘቡ በሚያወጣው ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን የሰው ልጅ ወደ ሌሎች በሚደርስ መልኩ የሚሰራውና የሚናገረውን ሁሉ መልካም ነገሮችን ያቀፈ ነው።

በዚህ ሀዲስ ውስጥ ለመልካምና ለሌሎች ጥቅም ላለው ነገር ሁሉ መልፋትን ያነሳሳል።

ትንሽም እንኳን ብትሆን ከመልካም ነገር አንዳችም ማሳነስ እንደማይገባ እንረዳለን።

التصنيفات

የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች