إعدادات العرض
የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች
የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች
1- ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ! ቀብሬንም የሚጎበኝ የበአል ስፍራ አታድርጉት! ይልቅ በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ! የትም ብትሆኑ ሶለዋታችሁ ትደርሰኛለችና።
2- ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።
4- ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።
6- ሁለት ሴት ልጆችን እስኪደርሱ ድረስ የተንከባከበ ሰው የትንሳኤ ቀን እኔና እሱ እንዲህ ሆነን ይመጣል።" ጣታቸውንም አጣበቁ።
8- ጌታችሁን አላህ ፍሩ፣ አምስት (አውቃት) ሶላታችሁን ስገዱ ፣ የፆም ወራችሁን ፁሙ፣ የገንዘባችሁንም ዘካ ስጡ፣ መሪያችሁን ታዘዙ፤ የጌታችሁን ጀነት ትገባላችሁ።
9- አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?
10- እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።
13- ፀጉረ ጨብራራና ከበር ተገፍትሮ የሚባረር በአላህ ሲምል ግን አላህ ከመሃላው የሚያጠራው ስንትና ስንት ሰው አለ?!
15- በፈተና ወቅት አላህን ማምለክ ወደኔ እንደመሰደድ ነው።
16- ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።
