ጌታችሁን አላህ ፍሩ፣ አምስት (አውቃት) ሶላታችሁን ስገዱ ፣ የፆም ወራችሁን ፁሙ፣ የገንዘባችሁንም ዘካ ስጡ፣ መሪያችሁን ታዘዙ፤ የጌታችሁን ጀነት ትገባላችሁ።

ጌታችሁን አላህ ፍሩ፣ አምስት (አውቃት) ሶላታችሁን ስገዱ ፣ የፆም ወራችሁን ፁሙ፣ የገንዘባችሁንም ዘካ ስጡ፣ መሪያችሁን ታዘዙ፤ የጌታችሁን ጀነት ትገባላችሁ።

ከአቡ ኡማማ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመሰናበቻ ሐጅ ወቅት እንዲህ ብለው ኹጥባ ሲያደርጉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "ጌታችሁን አላህ ፍሩ፣ አምስት (አውቃት) ሶላታችሁን ስገዱ ፣ የፆም ወራችሁን ፁሙ፣ የገንዘባችሁንም ዘካ ስጡ፣ መሪያችሁን ታዘዙ፤ የጌታችሁን ጀነት ትገባላችሁ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሂጅራ አስረኛው ዓመት በመሰናበቻው ሐጅ ወቅት የዐረፋ ቀን ኹጥባ አደረጉ። በዚህ ስያሜ የተሰየመችው እርሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ ወቅት ሰዎችን ስለተሰናበቱ ነው። ሰዎች ባጠቃላይ ትእዛዛቱን በመፈፀም ክልከላዎቹን በመራቅ ጌታቸውን እንዲፈሩ አዘዙ። በቀንና ምሽት አላህ ግዴታ ያደረገውን አምስት ሶላቶች እንዲሰግዱም አዘዙ። የረመዷንን ወርም እንዲፆሙ አዘዙ። የገንዘባቸውን ዘካ ለሚገባው ሰው እንዲሰጡና በርሱም እንዳይሰስቱ አዘዙ። በነርሱ ላይ አላህ መሪዎች ያደረጋቸውን አካላት አላህን በማመፅ እስካላዘዙ ድረስ ታዛዥ እንዲሆኑ አዘዟቸው። እነዚህን የተጠቀሱትን ጉዳዮች የፈፀመ ሰው ምንዳው ጀነት መግባት እንደሆነ ተናገሩ።

فوائد الحديث

እነዚህ ተግባራት ጀነት ከመግቢያ ሰበቦች መካከል ናቸው።

التصنيفات

የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች