አንድ ሰውዬ እየሄደ ሳለ መንገድ ላይ እሾካማ ቅርንጫፍ አገኘና አራቀው። አላህም ስራውን ተቀበለው። ወንጀሉንም ማረው።

አንድ ሰውዬ እየሄደ ሳለ መንገድ ላይ እሾካማ ቅርንጫፍ አገኘና አራቀው። አላህም ስራውን ተቀበለው። ወንጀሉንም ማረው።

ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሰውዬ እየሄደ ሳለ መንገድ ላይ እሾካማ ቅርንጫፍ አገኘና አራቀው። አላህም ስራውን ተቀበለው። ወንጀሉንም ማረው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና‐ አንድ ሰውዬ መንገድ ላይ ሙስሊሞችን በሚያውክ በእሾካማ ዛፍ ቅርንጫፍ በኩል ሲያልፍ ቅርንጫፉን ከመንገዱ እንዳራቀውና አላህም ስራውን ተቀብሎ ወንጀሉን እንደማረው ተናገሩ።

فوائد الحديث

የሚያውክን ነገር ከመንገድ ላይ የማራቅን ደረጃና ይህም አንዱ የአላህን ምህረት ማግኛ ምክንያት መሆኑን እንረዳለን።

መልካም ስራዎች ትንሽ እንኳ ቢሆኑ ማሳነስ እንደማይገባ እንረዳለን።

እስልምና የንፅህና፣ የማህበረሰብን ደህንነትና የህዝብን ሰላም የሚጠብቅ ሃይማኖት ነው።

التصنيفات

የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች