አላህ ለርሷ በዚህ ስራዋ ወይ ጀነትን ግድ አድርጎላታል፤ ወይም በዚህ ስራዋ ከእሳት ነፃ አውጥቷታል።" አሉ።

አላህ ለርሷ በዚህ ስራዋ ወይ ጀነትን ግድ አድርጎላታል፤ ወይም በዚህ ስራዋ ከእሳት ነፃ አውጥቷታል።" አሉ።

ከአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «አንዲት ሚስኪን ሴትዮ ሁለት ሴት ልጆቿን ተሸክማ እኔ ዘንድ መጣች። ሶስት ቴምሮችን ሰጠኃት። ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ ሰጠቻቸው። የቀረችውንም ተምር ራሷ ልትበላው ወደ አፏ ስታነሳ ሁለቱ ልጆቿም ጎመጁ ልትበላው ፈልጋ የነበረችውንም ተምር ለሁለት ሰነጠቀችና አካፈለቻቸው። ስራዋ እጅግ አስደንቆኝ ያደረገችውን ለአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) አወሳሁላቸው። እርሳቸውም "አላህ ለርሷ በዚህ ስራዋ ወይ ጀነትን ግድ አድርጎላታል፤ ወይም በዚህ ስራዋ ከእሳት ነፃ አውጥቷታል።" አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአማኞች እናት ዓኢሻ (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) እንዳወሳችው: አንድ ሚስኪን ሴት ሁለት ሴት ልጆቿን ተሸክማ ዓኢሻን ለመነቻት። ዓኢሻም ሶስት ቴምሮችን ሰጠቻት። ለእያንዳንዷ ልጆቿ አንድ አንድ ቴምር ሰጠችና አንዷን ቴምር ደግሞ ልትበላት ወደ አፏ አስጠጋች። ነገር ግን ልትበላት የፈለገቻትን አንዷን ቴምር ሁለቱ ልጆቿ መፈለጋቸውን ተረዳችና ያንኑም ቴምር ለሁለት ከፍላ አከፋፈለቻቸው። የሴትዬዋ ጉዳይም ዓኢሻን (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) ስለደነቃት ሴትዬዋ የሰራችውን ሁሉ ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነገረቻቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሏት: "አላህ በዚህች ተምር ምክንያት ወይ ጀነትን ግድ አድርጎላታል፤ ወይም ደሞ በዚህች ተምር ምክንያት ከእሳት ነፃ አድርጓታል።

فوائد الحديث

ምፅዋት ብታንስ እንኳ ያላትን ደረጃ እንረዳለን። ምፅዋት አማኝ በጌታው ላይ ያለው እምነት እውነተኛ እንደሆነና ጌታው በገባለት ቃልና ደረጃ መተማመኑን ይጠቁማል።

እናቶች ለልጆቻቸው ያላቸውን ከፍተኛ እዝነትና ልጆቻቸው እንዳይጎዱ ያላቸውን ስስት እንረዳለን።

ከነፍስ በላይ ሌላን ማስቀደም፣ ለህፃናት ማዘን፣ ለሴት ልጆች ሲሆን ደግሞ ተጨማሪ ደግነትና እዝነት ማሳየት ያለውን ደረጃና ይህም ጀነት ለመግባትና ከእሳት ነፃ ለመውጣት አንዱ ምክንያት እንደሆነ እንረዳለን።

ትንሽ ነገርን አሳንሶ በማየት አለመመፅወት አግባብ አይደለም። ይልቁንም ምፅዋት ሰጪው አነስም በዛ የገራለትን መመፀወት ይገባዋል።

ከዚህ ሐዲሥ ከምንወስዳቸው ቁምነገሮች መካከል የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤቶች የነበሩበት ተጨባጭ እንዴት እንደነበር የርሳቸውና የሚስቶቻቸው ኑሮ ምን ይመስል እንደነበር እንረዳለን። በወቅቱ ከተወሰኑ ወይም ከሶስት ተምር የበለጠ ቤታቸው የሚበላ እንዳልነበረ እንረዳለን።

التصنيفات

የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች