ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።

ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።

ከበራእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።"»

[ከሁሉም ሰነዶቹ አንፃር ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሁለት ሙስሊሞች በመንገድና መሰል ቦታ ተገናኝተው አንዱ ሌላኛውን በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተሰጣጡ ለነርሱ (ከቦታው) በአካል ወይም ከመጨባበጡ እጃቸውን ከማለያየታቸው በፊት ወንጀላቸው ይማራል ብለው ተናገሩ።

فوائد الحديث

በመገናኘት ወቅት መጨባበጥ እንደሚወደድና በዚህም ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

መናዊይ እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሱና ሌላ ችግር እስከሌለ ድረስ ቀኝ እጅን ቀኝ እጅ ላይ በማሳረፍ ካልሆነ በቀር አይገኝም።»

ሰላምታን በማብዛት ላይ መነሳሳቱንና አንድ ሙስሊም ሌላውን ሙስሊም ወንድሙ በመጨበጥ የሚያገኘው ምንዳ ትልቅነት መገለፁን እንረዳለን።

አጅነቢይ (ባዳ የሆነችን) ሴት መጨበጥ የመሰለው ክልክል የሆነ መጨባበጥ ከዚህ ሐዲሥ ውጭ ነው።

التصنيفات

የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች, የሰላምታና የማስፈቀድ ስነ-ስርዓት