إعدادات العرض
ፀጉረ ጨብራራና ከበር ተገፍትሮ የሚባረር በአላህ ሲምል ግን አላህ ከመሃላው የሚያጠራው ስንትና ስንት ሰው አለ?!
ፀጉረ ጨብራራና ከበር ተገፍትሮ የሚባረር በአላህ ሲምል ግን አላህ ከመሃላው የሚያጠራው ስንትና ስንት ሰው አለ?!
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦ "ፀጉረ ጨብራራና ከበር ተገፍትሮ የሚባረር በአላህ ሲምል ግን አላህ ከመሃላው የሚያጠራው ስንትና ስንት ሰው አለ?!"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî தமிழ் Nederlands Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી Magyar ქართული Română ไทย Português मराठी ភាសាខ្មែរ دریالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሰዎች መካከል ፀጉሩ አመዳም የሆነና የተቆጣጠረ፤ ቅባትም የማይቀባውና አብዝቶ የማይታጠበው፤ ሰዎች ዘንድ ቦታ ስለሌለው አሳንሰውም ስለሚያዩት ከበራቸው የሚገፈትሩትና የሚያባሩት አይነት ሰው እንዳለ ነገር ግን ይህ ሰው አንድ ነገር እንደሚከሰት ቢምል መሃላው እንዳይፈርስና በዛም ተጠያቂነት እንዳይመጣበት አላህ እርሱን በማክበር መሃላውን ከማፍረስ ሊታደገው ዘንድ ጉዳዩን ተቀብሎ የማለበት ነገር እንዲከሰት የሚያደርግለት ሰው ነው። ይህም አላህ ዘንድ ደረጃና ክብር ስላለው መሆኑን ብለው ተናገሩ።فوائد الحديث
አላህ የሚመለከተው የባሪያውን ቅርፅ ሳይሆን የሰራውን ስራና ቀልቡን ነው።
የሰው ልጅ በሰውነቱና በአለባበሱ ላይ ትኩረት ከሚያደርገው በላይ በስራውና ልቡን በማፅዳት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባዋል።
ለአላህ መተናነስና መዋደቅ ዱዓ ተቀባይነት እንዲያገኝ አንዱ ምክንያት ነው። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እርሱን የሚፈሩ ከሰው ደበቅ ያሉ ሰዎችን መሃላቸውን የሚያጠራው ለዛ ነው።
አንዱ አንዱን ዝቅ አድርጎ እንዳያይ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ለሰዎች ይሰጡት የነበረውን ነቢያዊ እነፃ ግልፅ መሆኑን ተረድተናል።
التصنيفات
የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች