ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።

ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።

ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ይሉ ነበር፡ "ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትላልቆቹን ወንጀሎች መጠንቀቅ እንደቅድመ መስፈርት ከተሟላ አምስቱ በቀንና ሌሊት የሚከናወኑት ሶላቶች፣ በየሳምንቱ የሚሰገደው የጁምዐ ሶላትና በየአመቱ የረመዳንን ወር መፆም በመካከላቸው የሚፈፀምን ትናንሽ ወንጀሎችን እንደሚያስምሩ ነገሩን። ዝሙትና መጠጥን የመሰሉ ከባባድ ወንጀሎች በተውባ ካልሆነ በቀር አይሰረዙም።

فوائد الحديث

ከወንጀሎች መካከል ከባባድና ትናንሽ የሚባሉ እንዳሉ እንረዳለን።

ትናንሽ ወንጀሎች የሚሰረዙት ከባባዶቹን ወንጀሎች መራቅን እንደመስፈርት ማሟላት ከተቻለ መሆኑን እንረዳለን።

ትላልቅ ወንጀሎች የሚባሉት ወይ በዱኒያ ቅጣት የተወሰነባቸው፣ ወይም በአኼራ የሚያስከትሉትን የቅጣት አይነት የተነገረባቸው፣ ወይም የአላህ ቁጣ የመጣባቸው፣ ወይም ከባድ ዛቻ ያለባቸው፣ ወይም ደግሞ አድራጊው የተረገመባቸው ሲሆኑ ነው። ለምሳሌ፡ ዝሙት፣ መጠጥ መጠጣት ይጠቀሳሉ።

التصنيفات

ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት, የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች, የሶላት ትሩፋት