ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ! ቀብሬንም የሚጎበኝ የበአል ስፍራ አታድርጉት! ይልቅ በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ! የትም ብትሆኑ ሶለዋታችሁ ትደርሰኛለችና።

ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ! ቀብሬንም የሚጎበኝ የበአል ስፍራ አታድርጉት! ይልቅ በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ! የትም ብትሆኑ ሶለዋታችሁ ትደርሰኛለችና።

አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል: የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ! ቀብሬንም የሚጎበኝ የበአል ስፍራ አታድርጉት! ይልቅ በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ! የትም ብትሆኑ ሶለዋታችሁ ትደርሰኛለችና።"

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ቤቶችን እንደ መቃብር ከሶላት የተገለሉ እና ሶላት የማይሰገድባቸው ከማድረግ እየከለከሉ ነው። እንዲሁም ልማድ አድርጎ በመያዝ የሳቸውን ቀብር ደጋግሞ መጎብኘቱንም እዚያው መሰብሰቡም ወደ ሽርክ ስለሚያደርስ ከለከሉ። ከዛ ይልቅ ወደ ቀብራቸው መመላለስ ሳያስፈልግ ቅርብም ይሁን ሩቅ እኩል ለእርሳቸው ስለሚደርሳቸው ከየትኛውም ቦታ ሆነን በሳቸው ላይ ሶለዋት እንድናወርድ አዘዙን።

فوائد الحديث

ቤቶች አሏህን ከማምለክ መገለላቸው የተከለከለ መሆኑ፤

የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ቀብር ለመዘየር አስቦ ጉዞ መውጣት መከልከሉን፤ ምክንያቱም ሶለዋት በሳቸው ላይ እንድናወርድና እንደሚደርሳቸውም ነግረውናልና። በአምልኮ መንፈስ ጉዞ የሚወጣው ወደ መስጂዱ ለመሄድና እዛው ለመስገድ ከሆነ ብቻ ነው።

በተለየ መልኩና በተለየ ጊዜ የርሳቸውን ቀብር ደጋግሞ መጎብኘትን ልምድ አድርጎ መያዝ መከልከሉ፤ የሌላን ቀብርም ቢሆን እንደዚሁ የተከለከለ ነው።

የላቀው አሏህ ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ጊዜ በሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድን መደንገጉ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አምላካቸው ዘንድ ያላቸውን ከፍተኛ ደረጃ ያሳያል።

መቃብር ዘንድ መስገድ መከልከሉ ሶሓቦች ዘንድ የፀና ጉዳይ በመሆኑ ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባልደረቦቻቸው ቤቶቻቸውንም እንደመቃብሩ የማይሰገድበት እንዳያደርጉ ከለከሏቸው።

التصنيفات

የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች, የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች