ሰውዬው ከሚያወጣው በላጩ ገንዘብ: ለቤተሰቦቹ የሚያወጣው ገንዘብ፣ ሰውዬው በአላህ መንገድ ለሚዘምትባት እንስሳ የሚያወጣው ገንዘብ፣ በአላህ መንገድ ለሚታገሉ ባልደረቦቹ የሚያወጣው…

ሰውዬው ከሚያወጣው በላጩ ገንዘብ: ለቤተሰቦቹ የሚያወጣው ገንዘብ፣ ሰውዬው በአላህ መንገድ ለሚዘምትባት እንስሳ የሚያወጣው ገንዘብ፣ በአላህ መንገድ ለሚታገሉ ባልደረቦቹ የሚያወጣው ገንዘብ ነው።

ከሠውባን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው ከሚያወጣው በላጩ ገንዘብ: ለቤተሰቦቹ የሚያወጣው ገንዘብ፣ ሰውዬው በአላህ መንገድ ለሚዘምትባት እንስሳ የሚያወጣው ገንዘብ፣ በአላህ መንገድ ለሚታገሉ ባልደረቦቹ የሚያወጣው ገንዘብ ነው። አቡ ቂላባህ እንዲህ አለ: በቤተሰብ ጀመሩ። ቀጥሎም አቡ ቂላባህ እንዲህ አለ "በታዳጊ ቤተሰቦቹ ላይ መፅውቶ የሚያብቃቃቸው ወይም አላህ በርሱ የሚጠቅማቸውና የሚያብቃቃቸው ከሆነ ሰውዬ የበለጠ ማንኛው ሰው ነው ትልቅ ምንዳ የሚያገኘው?!"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመመፅወት አቅጣጫዎችን ገለፁ። የሚመፀወትባቸው አቅጣጫዎች የተደራረቡ ጊዜም በእርሶ ላይ ግዴታ ከሚሆነው አንፃር ቅደም ተከተሉ ገለፁ። እጅግ አንገብጋቢና ወሳኝ በሆነውም ጀመሩ። እጅግ በጣም ብዙ ምንዳ የሚያስገኘው ገንዘብ አንድ ሙስሊም ወጪ ግዴታ ለሆነባቸው የሚመፀውተው ገንዘብ እንደሆነ ገለፁ። ለምሳሌ ሚስት፣ ልጅና የመሳሰሉት ቀጥሎ በአላህ መንገድ ለሚደረግ ጦርነት ለተዘጋጀ መጓጓዣ የሚወጣ ወጪ ነው። ቀጥሎም በአላህ መንገድ የሚታገሉ ለሆኑ ጓደኞቹና ባልደረቦቹ መመፅወት ነው።

فوائد الحديث

የምፅዋት ደረጃ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ቅደም ተከተል መደረጉንና የምናወጣባቸው ጉዳዮች በተደራረቡ ጊዜ ይህን ቅደም ተከተል መጠበቅ እንዳለብን እንረዳለን።

ለቤተሰብ የሚወጣ ወጪ በደረጃ ከሌሎች ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑ መገለፁን እንረዳለን።

በአላህ መንገድ ለሚደረግ ትግል መመፅወት ከትላልቅ ምፅዋቶች አንዱ ነው። ለምሳሌ ያህል ለጂሃድ መሳሪያና ሙእሚኖችን ለማስታጠቅ መመፅወት ይጠቀሳል።

በአላህ መንገድ በማለት የተፈለገው ሁሉም ትእዛዛቶችን ነው ያሉም አሉ። ለምሳሌ ለሐጅ ወጪ ማድረግ ነው።

التصنيفات

የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች, የአካል ተግባራት ትሩፋቶች