ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።

ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።

ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቅርብ ዘመዶችን በመዘየር ፣ በአካላዊና ገንዘባዊ ጉዳይ በማገዝና በሌሎችም መልኩ ዝምድናን በመቀጠል ላይ አነሳሱ። በተጨማሪም ዝምድናን መቀጠል ለሲሳይ መስፋትና ለእድሜ መርዘም ምክንያት መሆኑንም ተናገሩ።

فوائد الحديث

ዝምድና በማለት የተፈለገው በአባትና በእናት በኩል ያሉ ቅርብ ሰዎች ናቸው። እጅግ ቅርብ ዘመድ በሆኑ ቁጥር በዛው ልክ መቀጠሉም የተገባ ይሆናል።

ምንዳ በስራው አምሳያ ነው የሚሰጠው። ዝምድናውን በበጎና መልካምነት የቀጠለ ሰውን አላህም እድሜውና ሲሳዩን ይቀጥልለታል።

ዝምድናን መቀጠል ለሲሳይ መስፋትና መዘርጋት እንዲሁም ለእድሜ መርዘም ምክንያት ነው። ምንም እንኳ የመሞቻ ቀኑና ሲሳዩ የተወሰነ ቢሆን ባለው ሲሳይና እድሜ በረከት ይሰፍንበታል። የተሰጠውን እድሜ ሌላው ከሚጠቀምበት በላይ ይጠቀምበታል። በርግጥ የሲሳይና እድሜ መጨመሩ እውነተኛ መጨመር ነውም ተብሏል። አላህ እጅግ አዋቂ ነው!

التصنيفات

የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች