إعدادات العرض
አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?
አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?" ሶሐቦችም "እንዴታ የአላህ መልክተኛ" አሉ። እርሳቸውም "በአስቸጋሪ ወቅት ዉዱእን አዳርሶ ማድረግ፣ ወደ መስጂድ እርምጃ ማብዛት፣ አንድ ሰላት ካለቀ በኋላ ሌላኛው ሶላት መጠበቅ፤ ይሀው ነው "ሪባጥ" (ዘብ መጠበቅ) ናቸው።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල دری অসমীয়া ไทย Svenska Кыргызча Yorùbá ગુજરાતી नेपाली മലയാളം Oromoo Română Nederlands Soomaali پښتو తెలుగు Kinyarwanda Malagasy ಕನ್ನಡ Српскиالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለወንጀሎቻቸው መማር፣ ከጠባቂ መላዕክት መዝገብ ወንጀላቸውን ለማሰረዝ፣ በጀነት ውስጥም ደረጃዎችን ከፍ ለማድረግ ምክንያት የሚሆኑ ስራዎችን እንዲጠቁሟቸው ይፈልጉ እንደሆነ ባልደረቦቻቸውን ጠየቋቸው። ሶሐቦችም: "አዎን እንፈልጋለን" አሉ። እሳቸውም እንዲህ አሉ: የመጀመሪያው: እንደ ቅዝቃዜ፣ የውሃ ማነስ፣ የሰውነት ህመምና አቃጣይ ውሃን የመሰሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙም ዉዱእን መሙላትና ማዳረስ ነው። ሁለተኛው: እርምጃን ከሩቅ አካባቢ ወደ መስጂድ ማብዛትና ደጋግሞ መመላለስ ነው። ሶስተኛ: የሶላትን ወቅት መጠበቅ፣ ልብን በሶላት ማንጠልጠል፣ ለሶላት መዘጋጀት፣ ጀመዓን ለመጠበቅ መስጂድ ውስጥ ለሶላት መቀመጥ፣ ከሰገደም በኋላ ለሌላ ሶላት መስገጃው ላይ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ነው። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚህ ጉዳዮች ትክክለኛው ዘብ መጠበቅ እንደሆኑ ገለፁ። ምክንያቱም የሰይጣንን መንገዶች በነፍስ ላይ ስለምትዘጋ፣ ስሜትን ስለምታሸንፍ፣ ነፍስ ለወስዋስ ተገዥ እንዳትሆን ስለምትከለክል ነው። ነፍስን በማሸነፍ የአላህ ጭፍራ የሰይጣንን ሰራዊት ያሸንፉበታል። ትልቁ ጂሀድም ይህ ነው። ስለዚህ ይህ ድንበር ኬላ ላይ ጠላትን በመጠበቅ ደረጃ እንደሆነ አድርገው ገለፁት።فوائد الحديث
መስጂድ ውስጥ የህብረት ሶላትን የመጠባበቅ አንገብጋቢነቱን፤ ለሶላት ትኩረት መስጠትና ከሶላት በሌላ ነገር መጠመድ እንደሌለብንም እንረዳለን።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስራው የሚያስገኘውን ትልቅ ምንዳ በጥያቄያዊ መንገድ አስቀድመው ባልደረቦቻቸውን በማጓጓታቸው የትምህርት አቀራረባቸውን ማማር እንረዳለን። ይህም አንዱ የማስተማሪያ መንገድ ነው።
አንድን ጉዳይ በጥያቄና መልስ መንገድ ማቅረብ ብይኑን መጀመሪያ በመደበቅና ቀጥሎ በማብራራት ንግግሩ ነፍስ ውስጥ እንዲቀር የማድረግ ጥቅም አለው።
ነወዊ አላህ ይዘንላቸውና «ይህ ነው "ሪባጥ" (ዘብ መጠበቅ)» ማለት ተፈላጊው ዘብ መጠበቅ ይህ ነው ማለት ነው። ሪባጥ የሚለው ቃል መሰረት በአንድ ነገር ላይ መታጠር ማለት ሲሆን በነዚህ ስራዎች አላህን በመገዛት ላይ ነፍሱን ስለሚያጥር ነው። "ጂሃድ ማለት ነፍስን መታገል ነው።" እንደሚባለው በላጩ ሪባጥ ይህ ነውም ተብሏል። በሌላ አባባል ደሞ ቀላሉና የሚመቸው ሪባጥ ነው ማለት ተፈልጎበት ሊሆንም ያስመቻል። ማለትም ከሪባጥ አይነቶች አንዱ ነው እንደማለት ነው።
(አል) የምትለዋ ገላጭ ገብታ "አር‐ሪባጥ" የምትለዋ ቃል መደጋገሟ የነዚህ ስራዎችን ትልቅነት ያስረዳናል።
التصنيفات
የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች