እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ ጀነት ትገባላችሁ በሰላም።

እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ ጀነት ትገባላችሁ በሰላም።

ከዐብደላህ ቢን ሰላም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መዲና የገቡ ጊዜ ሰዎች ወደርሳቸው በፍጥነት ሄዱ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ ‐ ሶስት ጊዜ ‐ እየተባለ ተወራ። ለመመልከትም ከሆኑ ሰዎች ጋር መጣሁ። ፊታቸውን የተመለከትኩኝ ጊዜ ፊታቸው የውሸታም ፊት እንዳልሆነ አወቅኩ። መጀመሪያ ሲናገሩ የሰማሁት ነገር እንዲህ ሲሉ ነው: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ ጀነት ትገባላችሁ በሰላም።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል። - ቲርሚዚ ዘግበውታል። - አሕመድ ዘግበውታል። - Ad-Daarimi]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መዲና መጥተው ሰዎች የተመለከቷቸው ጊዜ ወደርሳቸው አቅጣጫ በፍጥነት ሄዱ። ዐብደላህ ቢን ሰላምም ያኔ አይሁድ ነበርና ወደርሳቸው ከመጡት መካከል አንዱ ነው። እርሳቸውን ሲያይም በርሳቸው ላይ ብርሃንን፣ ውበትንና እውነተኛ ግርማን በማየቱ ፊታቸው የውሸታም ፊት እንዳልሆነ አወቀ። ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንደበት ለመጀመሪያ የሰማውም ነገር ሰዎችን ጀነት ለመግባት ሰበብ የሚሆናቸውን ተግባራት ላይ ማነሳሳታቸውን ነው። መጀመሪያ: ባወቅከውም ይሁን ባላወቅከውም ሰው ላይ ሰላምታን ማሰራጨት፣ ከፍ ማድረግና ማብዛት ነው። ሁለተኛ: ምግብን በሶደቃ፣ በስጦታና በእንግድነት መልክ ማብላት ነው። ሶስተኛ: በአባት ወይም በእናት በኩል ቅርበትና ዝምድና ከምታስተሳስርህ አካል ጋር ዝምድናን መቀጠል ነው። አራተኛ: ሰዎች በተኙበት ለሱና (ግዴታ ላልሆነ) ሶላት ሌሊት መቆም ነው።

فوائد الحديث

በሙስሊሞች መካከል ሰላምታን ማሰራጨት እንደሚወደድ እንረዳለን። ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን ግን (አሰላሙ ዓለይኩም) በሚል ሰላምታ አይጀመሩም። ሙስሊም ያልሆነ ሰው ራሱ "አሰላሙ ዐለይኩም" በማለት ሰላምታን ካቀረበ "ወዐለይኩም" በማለት ይመልስለታል።

التصنيفات

የሌሊት ሶላት መስገድ, የመልካም ስራዎች ትሩፋቶች