ከኔ በኋላ ወንዶች ላይ ከሴት የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተና አልተውኩም።

ከኔ በኋላ ወንዶች ላይ ከሴት የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተና አልተውኩም።

ከኡሳማህ ቢን ዘይድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ከኔ በኋላ ወንዶች ላይ ከሴት የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተና አልተውኩም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሳቸው በኋላ በወንዶች ላይ ከሴቶች የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተናና መሞከሪያ እንዳልተዉ ተናገሩ። ከቤተሰቡ አባላት ከሆነች ሸሪዓን ከሚፃረር መንገድ ላይ እሷን የመከታተል ጣጣው ይገኝበታል። ባዳ ከሆነች ደግሞ ከሷ ጋር በመቀላቀልና ለብቻቸው በመገለል በርሱ ሳቢያ ብልሽቶችን የሚያመጡ ነገሮችን በመፈፀም ነው።

فوائد الحديث

ሙስሊም የሆነ ሰው የሴቶችን ፈተና መጠንቀቅና በርሷ ወደ መፈተን የሚያደርሰውን መንገዶችን ሁሉ መዝጋት ይገባዋል።

አንድ አማኝ በአላህ መጠበቅና ከፈተና ነፃ እንዲያደርገውም ወደርሱ መከጀል ይገባዋል።

التصنيفات

ከዝንባሌና ስሜት ማውገዝ