إعدادات العرض
እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።
እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።
ከሙጊራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "አንድ ጉዞ ላይ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩና ኹፋቸውን (የቆዳ ካልሲያቸውን) ላወልቅ ዝቅ አልኩ፤ እሳቸውም: ' እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።' አሉኝና በነርሱ ላይ አበሱ።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî മലയാളം Kiswahili Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá සිංහල ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or नेपाली Malagasy Română Kinyarwanda తెలుగు Lietuvių Oromoo Nederlands Soomaali Shqip Српски Deutsch Українська ಕನ್ನಡ Wolof Moore ქართული Azərbaycan Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአንድ ጉዟቸው ላይ ሳሉ ዉዱእ አደረጉ። ሁለት እግራቸውን ማጠብ ላይ በደረሱ ጊዜ ሙጚራ ቢን ሹዕባ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እግራቸውን እንዲያጥቡ ብለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አድርገውት የነበረውን ኹፍ ሊያወልቁ እጃቸውን ዘረጉ ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "አታውልቃቸው ተዋቸው! እኔ ሁለት እግሬን ኹፎቹ ውስጥ ያስገባሁት በጦሀራ ላይ ሁኜ ነው " አሏቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እግራቸውን በማጠብ ምትክ ኹፋቸውን አበሱ።فوائد الحديث
ሁለት ኹፎች ላይ ማበስ የተደነገገው ከትንሹ ሐደሥ (ዉዱእ አጥፍቶ) ዉዱእ በሚደረግበት ወቅት ነው። ለትልቁ ሐደሥ (ገላን ለሚያስታጥብ ጉዳይ) መታጠብ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ግን የግድ ሁለት እግሮችን መታጠብ ይኖርበታል።
ኹፍ ላይ ማበስ የሚገኘው በውሃ በረጠበ እጅ ታችኛውን ሳይሆን ላይኛውን የኹፉ ክፍል አንድ ጊዜ በመዳበስ ነው።
በሁለት ኹፎች ላይ ለማበስ ሊሟሉ የሚገቡ መስፈርቶች አሉ። እነሱም: ኹፎቹን የሚለብሰው ሁለት እግሮቹን በውሃ ካጠበበት የተሟላ ዉዱእ በኋላ መሆን ይገባዋል፤ ኹፉ ንፁህና በትጥበት ወቅት ማጠብ ግዴታ የሆነውን የእግሩን ክፍል የሸፈነ መሆን ይገባዋል፤ የሚያብሰው በጀናባ (የዘር ፈሳሽ መጥቶት ወይም ግንኙነት በማድረጉ) ወይም ገላን የሚያስታጥቡ ነገሮች ሲያጋጥሙት ሳይሆን በትንሹ ሐደሥ (ውዱእ የሚያስደርጉ ምክንያቶች ሲያጋጥሙት) ብቻ መሆን ይገባዋል፤ የሚያብሰውም በሸሪዓ በተወሰነው ወቅት መሆን ይገባዋል። እሱም መንገደኛ ላልሆነ አንድ ቀን ከነምሽቱ ሲሆን ጉዞ ላይ ላለ ደግሞ ሶስት ቀን ከነሌሊቱ ነው።
እንደካልሲና የመሳሰሉት ሁለት እግሮችን የሚሸፍኑ ሁሉ እንደ ሁለቱ ኹፎች ተመሳሳይ ፍርድ ስላላቸው በነርሱ ላይም ማበስ ይበቃል።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙጚራ ኹፋቸውን እንዳያወልቅ ሲከለክሉት ነፍሱ እንድትረጋጋና ብይኑን እንዲያውቅ ምክንያታቸውን መግለፃቸው የርሳቸው ስነምግባርና የማስተማር መንገዳቸው ማማሩን ያስረዳናል።