ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።

ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካምስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል: "ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።"

[ሐሰን ነው።] [ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአምልኮዎች መካከል ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ እጅግ በላጭ የሆነ አምልኮ አንድም እንደሌለ ገለፁ። ምክንያቱም ዱዓእ የአላህን መብቃቃት፣ የባሪያን ደካማነትና ፈላጊነት እውቅና መስጠትን ውስጡ ይዟልና ነው።

فوائد الحديث

የዱዓእን ትሩፋት እንረዳለን። አላህን የለመነ ሰው አላህን እያላቀ፣ የሌለው አይከጀልምና ጥራት የተገባው አምላክ እጅግ የተብቃቃ መሆኑን፣ ደንቆሮ አይለመንምና እጅግ ሰሚ መሆኑን፣ ስስታም አይለመንምና ቸር መሆኑን፣ ልበደረቅ አይለመንምና አዛኝ መሆኑን፣ ደካማ አይለመንምና ቻይ መሆኑን፣ ሩቅ ያለ አይሰማምና ቅርብ መሆኑን እና ሌሎችም የልቅናና የምሉዕነት መገለጫዎችን ለአሏህ እያረጋገጠ ነው።

التصنيفات

የዱዓእ ትሩፋቶች