إعدادات العرض
1- እርሱ ዘንድ ስሜ ተወስቶ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ረመዷንን አግኝቶ ከዚያም ከመማሩ በፊት የወጣበት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ወላጆቹን እርጅና ላይ አግኝቶ ጀነት ያላስገቡት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ።
2- ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።
3- የአደም ልጆች ቀልቦች ሁሉ ከአርራሕማን ጣቶች በሁለቱ ጣቶች መካከል ናቸው። (እርሱ ዘንድ ሁሉም ቀልቦች) እንደ አንድ ቀልብ ናቸው። እንደፈለገ ይገለባብጣቸዋል።
4- አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!
5- ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።
6- አማኞች ጀነት ውስጥ ከአንድ ወጥና ውስጡ ባዶ ከሆነ ሉል የተሰራ ድንኳን አላቸው። ርዝማኔውም ስልሳ ማይል ነው። ለአማኞችም በውስጡ ሚስቶች አሏቸው። አንድ አማኝ እነርሱን (ሊገናኝ) ይዞራል። ነገር ግን እርስበርሳቸው አይተያዩም።
7- አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: "ደጋግ ለሆኑ ባሪያዎቼ ዓይን ያላየችው፤ ጆሮ ያልሰማችው፤ በሰው ቀልብ ላይ ውል ያላለን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።
8- ከፀያፍ ቃላትም ይሁን ድርጊት የራቁ ነበሩ፤ በየገበያው የሚጮሁም አልነበሩም፤ መጥፎንም በመጥፎ የሚመልሱ አልነበሩም። ይልቁንም መጥፎን ይቅርታ በማድረግና ችላ ብሎ በማለፍ ነበር የሚመልሱት።
9- ቀብር የመጪው ዓለም የመጀመሪያው ማረፊያ ነው። ከቀብር (ቅጣት) ከዳነ ከቀብር በኋላ ያለው ከርሱ የበለጠ ቀላል ነው። ከቀብር (ቅጣት) ካልዳነ ከቀብር በኋላ ያለው ቅጣት ከርሱ የበረታ ነው።
10- የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጎ ላደርግለት እጅግ የተገባው ማን ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም አባትህ ከዚያም ቅርብ የሆኑ ዘመዶችህ" አሉ።
11- ጀነት የሚገባው የመጀመሪያው ስብስብ ጨረቃ ሙሉ የምትሆንበትን (የለይለቱል በድርን) አይነት ውበት ይዘው ነው። ቀጥለው የሚገቡት ደግሞ የሚያበሩት ሰማይ ላይ እንዳለ እጅግ ትልቅ ኮኮብ መስለው ነው።
12- አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት።
13- ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ምንዳ ቢያውቁና እርሱንም እጣ ካልተጣጣሉ በቀር የማያገኙት ቢሆን ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር።
14- በአላህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት ወድጃለሁ ያለ ሰው ጀነት ለርሱ ፀንታለታለች።
15- ነፍሱን ከተራራ ላይ ጥሎ የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ሲምዘገዘግ ይኖራል።
16- በአላህ ላይ አንዳችንም ላታጋሩ፤ ላትሰርቁ፤ ዝሙት ላትሰሩ፤
17- እስልምና እንግዳ ሆኖ ጀመረ። ልክ እንደጀመረውም ወደ እንግዳነት ይመለሳል። ለእንግዶቹ 'ጡባ' ይሰጣቸዋል (አለላቸው)።
18- ትናንሽ ተደርገው የሚታዩ ወንጀሎችን ተጠንቀቁ!
19- እኔ የተላኩት መልካም ስነምግባርን ላሟላ ነው።
20- ሰባት አካላቶች ከአላህ ጥላ በቀር ጥላ በሌለበት ቀን አላህ በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል።
21- ማንኛውም ለወንድሙ ‹አንተ ከሀዲ› ያለ ሰው በርግጥም በርሷ (በከሀዲነቷ) ላይ አንዳቸው ወድቀዋል። እንዳለው ሆኖ ከሆነ (መልካም) ያለበለዚያ ወደርሱ ትመለሳለች።
22- አላህ ዐዘ ወጀል እንዲህ አለ: ‹የአደም ልጅ ዘመንን በመሳደብ ያውከኛል። ዘመን እኔው ነኝ ፤ ነገሮች በኔ እጅ ናቸው፤ ምሽቱንና ቀኑን የምገለባብጠው እኔ ነኝ።›