ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ምንዳ ቢያውቁና እርሱንም እጣ ካልተጣጣሉ በቀር የማያገኙት ቢሆን ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር።

ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ምንዳ ቢያውቁና እርሱንም እጣ ካልተጣጣሉ በቀር የማያገኙት ቢሆን ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ምንዳ ቢያውቁና እርሱንም እጣ ካልተጣጣሉ በቀር የማያገኙት ቢሆን ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር። (ወደ መስጊድ) ማልዶ የመሄድን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ ለርሱ ይሽቀዳደሙ ነበር። የዒሻና ሱብሒን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳኹም ቢሆን ይመጡ ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ የሚገኘውን ደረጃ፣ መልካምና በረከት ቢያውቁ ኖሮና ከዚያም ለመቀደምና ቅድሚያ ለማግኘት ማነው የሚገባው ለሚለው እጣ መጣጣል ቢጠበቅባቸው ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር። ወደ ሶላት በመጀመሪያ ወቅት ቀድሞ የመሄድንም ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ ይሽቀዳደሙ ነበር። ወደ ዒሻ ሶላትና ወደ ፈጅር ሶላት መስጂድ የመምጣት ምንዳ መጠኑን ቢያውቁ ኖሮና ወደ መስጂድ መምጣት ቀላል ባይሆንላቸው ኖሮ ህፃን ልጅ እየዳኸ እንደሚመጣው በጉልበታቸው እየዳኹም ይመጡ ነበር አሉ።

فوائد الحديث

የአዛን ደረጃ መገለፁ፤

ወደ ኢማም መቅረብና የመጀመሪያ ሰልፍ ያለው ደረጃ መገለፁ፤

ሶላት ለመስገድ ተወዳጅ በሆነው በመጀመሪያ ወቅት ወደ መስጂድ ቀድሞ መሄድ ያለው ደረጃ መገለፁን እንረዳለን። ይህም ትልቅ ደረጃ ስላለውና እርሱን ተከትሎ በርካታ ጥቅሞች ስለሚገኝ ነው። ከነዚህ ጥቅሞች መካከልም: የመጀመሪያን ሰልፍ ማግኘት፤ ሶላት ላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ መድረስ፤ ሱናን መስገድ፤ ቁርአን መቅራት፤ መላእክቶች ለርሱ ምህረት ይጠይቁለታል፤ ሶላት እስኪደርስ እስከተጠባበቀ ድረስም ሶላት ላይ ከመሆን አለመወገድን፤ ከዚህም ውጪ ያሉ ጥቅሞችን ያገኛል።

እነዚህን ሁለት ሶላቶች በህብረት ለመስገድ በመገኘት ላይ መነሳሳቱንና በዚህም ብዙ ትሩፋት እንደሚገኝ እንረዳለን። ይህ ብዙ ትሩፋት የሚገኘውም በመጀመሪያ ወቅትና በመጨረሻው ወቅት ያለውን የእንቅልፍ ሰአት በማደፍረሱ ነፍስን ስለሚከብዳት ነው። ስለዚህም በሙናፊቆች ላይ ከባዳቹ ሶላቶች እነርሱ ሆኑ።

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በሚያጨቃጭቅና ሰው በሚበዛበት ሐቆች ላይ እጣ መጣጣል እንደሚቻል ያፀድቅልናል።"

ሁለተኛው ሰልፍ ከሶስተኛው፣ ሶስተኛው ደግሞ ከአራተኛው ሰልፍ ይበልጣል።

التصنيفات

ደረጃ ያላቸው ስራዎች, የሶላት ሱናዎች